የካፍ ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

የካፍ ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
ፕሬዚዳንቱ ረቡዕ ዕለት ከሞሮኮ ወደ ካይሮ ከተመለሱ በኋላ ቀለል ያለ የሳል ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ በተደረገላቸው ምርመራ በዛሬው ዕለት በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል።
በመሆኑም ፕሬዚዳንቱ ቢያንስ ለቀጣዮቹ 14 ቀናት በሆቴላቸው ራሳቸውን አግልለው እንደሚቆዩ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
እንዲሁም ባለፉት ሰባት ቀናት በተለይ በሞሮኮ በነበራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ራሳቸውን እንዲያሳውቁ እና አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ተጠይቋል።

The post የካፍ ፕሬዚዳንት አህመድ አህመድ በኮሮና ቫይረስ ተያዙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply