የካፒታል ገበያ ነገር፡-

የካፒታል ገበያ ወደስራ መግባቱን ተከትሎ በካፒታል ገበያው ውስጥ ስላለው የኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ዋና ተግባራት ከፕራግማ ኢንቨስትመንት አማካሪ ዋና ስራ አስፈፃሚ ከአቶ መርዕድ ብርሀን ጋር የተደረገ ቆይታ።

የኢንቨስትመንት ባንክ ማለት ምን ማለት ነው?

በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አዋጅ ቁጥር 1248/2021 አንቀፅ 34 መሰረት ኢንቨስትመንት ባንክ ተቀማጭ ገንዘብ የማይሰበስብ የገንዘብ ተቋም ነው፡፡

በግልም ይሁን በመንግስት የሚሸጡ የሰነደ መዋዕለ ነዋይ ሽያጮችን በውክልና የሚሸጥ ገዢ እና ሻጭን የማገናኘት ስራ የሚሰራ ተቋም እንደሆነም አቶ መርዕድ ይገልፃሉ።

ኢንቨስትመንት ባንክ የአማርኛ ፍቺው መዋዕለ ነዋይ ባንክ ሲሆን በሰነደ መዋዕለ ገበያ ውስጥ ሰነደ መዋዕለ ነዋይ አቅራቢዎችን ከገዢዎች ጋር በማድረግ የግብይት ስርዐቱ እንዲፋጠን የሚያደርግ ተቋም ነው።

የኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ዋና ተግባራት ምን ምን ናቸው ?

  • የመዋዕለ ነዋይ ገበያው አማካሪ በመሆን ያገለግላል ይህም ማለት ድርጅቶች በካፒታል ገበያው ውስጥ ጥሩ ሆነው እንዲቀርቡ ማብቃት
  • የሰነደ መዋዕለ ነዋዮችን የመግዛት እና የማሻሻጥ ስራም ይሰራል በዚህም ሰነዶችን ቀድሞ በመግዛት ለድርጅቶች የማከፋፈል ስራ ይሰራል
  • የድርጅቶችን ሰነዶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከገዢ ጋር እንዲገናኙ ሰነዱን ያዘጋጃል
  • እንዲሁም ለድርጅቶች ትላልቅ የሆነ የብድር ሰነዶችን በማገናኘት ብድር ያመቻቻሉ፡፡

አንቨስትመንት ባንክ ከሌሎች ባንኮች የሚለይባቸው ባህሪያትስ ምን ምን ናቸው

ንግድ ባንክም ይሁን የግል ባንኮች ተጠሪነታቸው ለብሄራዊ ባንክ ሲሆን የኢንቨስትመንት ወይም የሰነድ መዋዕለ ባንክ ተጠሪነት ግን ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ሲሆን የሚመራውም በካፒታል ገበያው ነው።

ሌሎች ባንኮች ውስጥ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ሲሆን ኢንቨስትመንት ባንክ ውስጥ ግን ተቀማጭ የሚሆነው ከሌሎች ባንኮች በተለየ መልኩ ሰነድ እንደሆነ አቶ መርዕድ ያስረዳሉ

ኢንቨስትመንት ባንክ የሰነደ መዋለ ነዋይነ ገዢ እና ሻጭን ከማገናኘት ባለፈም በካፒታል ገበያው ውስጥ ጥናት በማዘጋጀት ለድርጅቶች የማቅረብ ሂደት መሰራቱም ልዩ እንደሚያደርገውም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ከእቅዱ ቀድሞ ለማሰባሰብ ካቀደው የመመስረቻ ካፒታል በላይ መሰብሰቡን ሲነሳ መስራች የሚያደርገው የአክሲዮን ሽያጭ ቀነ ገደብም በቅርቡ እንሚጠናቀቅም በውይይቱ ተነስቷል።

በለዓለም አሰፋ

መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply