የኬንያ መንግሥት በተለያዩ ምርቶች ላይ ሊጥል የነበረው ቀረጥ ከሕዝብ በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ የአገሪቱ ፓርላማ በከፊል ውድቅ አደረገው።መንግሥት ተግባራዊ ሊያደርገው የነበረው የፋይናንስ ሕግ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/hKHh1uu102codMOr45WN5HrjfAdkzBBzOG6CCW7QpbOVT1ncbBTWvQigKjUR6-B3vUowcOX6D9aPcrPuCaZG20D8e516KRnmSg3lhdTPVGjUuvUWz-XD-kBh44PDfoZUs-72UzI9MmHXr_Cx6LWnYBxPvlGRu9F5SsgWoDUqmLBJYZxa8cTQMMCGJaF1LIwq_eDE58Syy46z2CFTGKiAvOOZDK_-sGfxecRfW21xMpMJStnubfv862mEg8t4tJW-DGNTunW2-z1scxEjjnB8ly1XeU0dGPg7Lv6_9xqrxU57RVB8oLv0hygS2LMTtWt0WQBoNPoC5gGfLVs8-fD7EA.jpg

የኬንያ መንግሥት በተለያዩ ምርቶች ላይ ሊጥል የነበረው ቀረጥ ከሕዝብ በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ የአገሪቱ ፓርላማ በከፊል ውድቅ አደረገው።

መንግሥት ተግባራዊ ሊያደርገው የነበረው የፋይናንስ ሕግ እንደ ዳቦ ባሉ ምርቶች ላይ እስከ 16 በመቶ ጭማሪን የሚያደርግ ነበር።

ረቂቅ ሕጉ ለአገሪቱ የተወካዮች ምክር ቤት ከተላከ በኋላ ኬንያውያን ወደ ምክር ቤቱ በማቅናት ጠንካራ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ትናንት ማክሰኞ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም. ፖሊስ ከፓርላማው ደጃፍ የተሰበሰቡ ተቃዋሚዎች በአስለቃሽ ጭስ ሲበትን የምክር ቤት አባላት በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት ሲያደርጉ ነበር።

ማክሰኞ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የሕግ ባለሙያዎችን ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ተቃዋሚዎቹ በታሰሩበት እስር ቤት አምርተው እንዲፈቱ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ጠይቀዋል።

እአአ 2022 ላይ ወደ ሥልጣን የመጡት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አገሪቱን ካለችበት የ80 በሊዮን ዶላር ዕዳ ለማውጣት እና ለዜጎች የሥራ ዕድልን ለመፍጠር በሚሉ ምክንያቶች የተለያዩ ግብሮችን ሲያስተላልፉ ቆይተዋል።

ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply