
በኬንያ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት ከተስፋ ይልቅ ስጋት የሚንጣቸው አካባቢዎች አሉ። ከእነዚህም መካከል ቢቢሲ የጎበኘው እና በመርሳቤት ከተማ አቅራብያ የሚገኘው መንደር ነዋሪዎች አንዱ ናቸው። ኬንያ በነሐሴ 3 2014 ዓ.ም ማክሰኞ፣ ለማካሄድ ቀጠሮ የያዘችለት ምርጫ ካለባቸው የደህንነት ስጋት ላይ ተጨማሪ ነዳጅ ያርከፈክፍ ይሆን የሚለው የስጋታቸው ምንጭ ነው።
Source: Link to the Post