ጥያቄያቸውም የኮቪድ-19ኝን መዘዝ ለመቋቋም የሚያስችል ለድሆች ያለመ በጀት ከመንግስት ይለቀቅልን የሚል ነው፡፡ህብረቱ የኬንያ ኢ-ፍትሂዊነትን አውጋዥ ህብረት የተሰኘ ነው፡፡ የድርጅቱና የአባላቱ ጥያቄም ኮቪድ-19 ክፉኛ የመታቸው ደሀ የማህበረሰብ ክፍሎች በልዩ በጀት ተጠቃሚ ይሁኑ የሚል ነው፡፡
በተለያዩ ዘርፎች ኢ-ፍትሃዊነት ነግሷል ይሄም እንዲስተካከል መንግስት ልዩ በጀት ለድሆች ሊመደብ ይገባል የሚለውን ጥሪ የሚመሩት የህብረቱ ዋና አስተባባሪ አንቶኒዮ ሙሱንጋ ናቸው፡፡በዚህ ምክንያትም የኬንያ ፓርላማ በድህረ-ኮቪድ ማገገሚያ ፖሊሲዎች ዙሪያ ለመወያየት አስቸኳይ ጉባኤውን ለማድረግ አባላቱን ጠርቷል፡፡
ይህ ከተሰማ በኃላ የኬንያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ህብረትና የደጋፊዎቹ እንቅስቃሴ ተቀጣጥሏል ሲል የዘገበው ዢንዋ ነው፡፡
ቀን 19/06/2013
አሐዱ ራድዮ 94.3
Source: Link to the Post