የኬንያ የንግድ ም/ቤት የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለመጠቀም እንደሚፈልግ ገለፀ

የኬንያ የንግድ ም/ቤት የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለመጠቀም እንደሚፈልግ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤቶች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ኤሪክ ሩቶ የኬንያ ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የንግድ ዕድሎችን መጠቀም እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያና ኬንያ በንግድና ኢንቨስትመንት ስትራቴጂካዊ ትስስር እንዳለ ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለኬንያውያን መልካም ጎረቤት ብቻ ሳትሆን ትልቅ ገበያ ናት ብለዋል፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባዘጋጀው የበይነ መረብ የቢዝነስ ውይይት ላይ በኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የውጭ ንግድና ቱሪዝም ማስፋፊያ ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ረጋሣ ከፋለ በመድረኩ  ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉትን የኢንቨስትመንት ዕድሎች በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሠጥተዋል፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው የሁለቱ ሃገራት የፖለቲካ ግንኙነት በኢኮኖሚ ትስስር መጠናከር እንዳለበት ጠቅሰዋል፡፡

አምባሳደር መለስ ዓለም  ኬንያ ለኢትዮጵያ ምርቶች መዳረሻ እንደሆነችና ከአንድ መቶ በላይ የኬንያ ባለሃብቶት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ መስኮች መሰማራታቸውን ገልፀዋል፡፡

መድረኩ ላይ የኢትዮጵያና ኬንያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የንግድ ምክር ቤቶች ከፍተኛ ባለስልጣናት እና  የሁለቱ አገራት ባለሀብቶች መሳተፋቸውን በኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

The post የኬንያ የንግድ ም/ቤት የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድሎች ለመጠቀም እንደሚፈልግ ገለፀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply