You are currently viewing “የክልሉ መንግስት አመራሮች ውጤት ሊያስገኝ የሚያስችል ትብብር ለሰላማዊ የሽምግልና ባሕላችን ባለማሳየታቸው እና ጉዳዩን በሽምግልና ለመጨረስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፤ ከተደጋጋሚ ፍሬ አልባ ሙከራ…

“የክልሉ መንግስት አመራሮች ውጤት ሊያስገኝ የሚያስችል ትብብር ለሰላማዊ የሽምግልና ባሕላችን ባለማሳየታቸው እና ጉዳዩን በሽምግልና ለመጨረስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፤ ከተደጋጋሚ ፍሬ አልባ ሙከራ…

“የክልሉ መንግስት አመራሮች ውጤት ሊያስገኝ የሚያስችል ትብብር ለሰላማዊ የሽምግልና ባሕላችን ባለማሳየታቸው እና ጉዳዩን በሽምግልና ለመጨረስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፤ ከተደጋጋሚ ፍሬ አልባ ሙከራዎች በኋላ የጀመርነውን የሽምግልና እንቀስቃሴ ያቆምን መሆኑን ስንገልጽ እጅጉን በማዘን ጭምር ነው።” በአርበኛ ዘመነ ካሴ ጉዳይ የተሰባሰቡ የአገር ሽማግሌዎች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 18 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአርበኛ ዘመነ ካሴ ጉዳይ የተሰባሰቡ የአገር ሽማግሌዎች የደረሱበትን ሂደት በሚከተለው መልኩ ይፋ አድርገዋል:_ ቀን፦ ሕዳር 18፣2015 ዓ/ም ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት፣ ለአብክመ ርእሰ መስተዳደር ጽ/ቤት፣ ለመላው የአማራ ሕዝብና ኢትዮጵያውያን፤ ጉዳዩ፦በአርበኛ ዘመነ ካሴ ጉዳይ የተሰባሰብን የአገር ሽማግሌዎች የደረሰንብትን ደረጃ ስለማሳወቅ፤ ሽማግሌዎች:_ 1. አቶ ሽባባው የኔኣባት፣ 2. ፕ/ር ይኸነው ገብረ ሥላሴ ፣ 3. ዶ/ር መኮንን አይችሉህም፣ 4. ዶ/ር ምንይችል ግታው፣ 5. አቶ በዛብነህ ጥሩነህ፣ 6. አቶ አበበ ይመኑ፣ 7. አቶ ሙሉጌታ ቢያዝን፣ 8. አቶ ደጉ አዲስ፣ 9. አቶ መሰረት አድነው፣ 1ዐ. አቶ አጣናው ቢረሳው፣ 1 1. አቶ ጥላሁን አሞኘ፣ 12. አስር አለቃ ዳኘ በየነ፣ 13. አቶ ጌታነህ ላቀው፣ 14.አቶ ሙላት ዘውዴ፣ 15. አቶ ተስፋሁን ተወዴ፣ 16. አቶ ተሰማ ሙሉነህ፣ 17. አቶ ክርሰቲያን ታደለ እና ሌሎችም እንደሚታወቀው መንግስት ከግንቦት ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ በዋናነት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ልዩ ልዩ ዞኖች በሚንቀሳቀሱ ፋኖዎች በተለይም አርበኛ ዘመነ ካሴ እና አጋሮቹን በሚመለከት የህግ ማስከበር ዘመቻ በሚል እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ከመሰከረም ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ አርበኛ ዘመነ ካሴም በእስር ላይ ይገኛል ፡፡ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ላለፉት 2 ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት ጨምሮ በኢትዮጵያ | ውስጥ የተፈጠሩ አለመግባባቶችን በድርድርና ሽምግልና ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ አቋም ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚበረታታ ጉዳይ ነው። እኛም የእነ አርበኛ ዘመነ ካሴን ጉዳይ በተከበረው የአገራችን አኩሪ የግጭት መፍቻ መንገድ በሆነው የሽምግልና ሥርዓት በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል። ይኽም እንቅስቃሴ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ከምክርቤት አባላት እነአርበኛ ዘመነን አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ጉዳዩ በሽምግልና እንዲያልቅ ግፉበት የሚል አበረታች ይሁንታን ያገኘ በመሆኑ፤ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳደሩን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ የቢሮ ኃላፊዎችና የካቢኔ አባላትን ለማነጋገር ከፍተኛ ጥረት ስናደርግ ቆይተናል፡፡ በዚህ ሂደትም ሽማግሌዎቹንም ሆነ የሽምግልና ሥርዓቱን በአክብሮት ተቀብለው በቀና መልኩ ያስተናገዱን ቢኖሩም አንዳንድ ባለሥልጣናት ግን በቢሮ ውስጥና በከተማ እያሉ፥ «የሉም» በማሰባል የሽምግልና ባሕላችንን በሚያራከስና በሚያዋርድ ሁኔታ ለማነጋገር እንኳ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ በዚህም ከፉኛ አዝነናል። ምንም እንኳ የሽምግልና ቡድኑ የተነሳበትን በጎ ዓላማ በውጤት ባይታጀብም የሕዝባችንን ነባር የሽምግልና እሴት አክብረው በወጉ ላስተናገዱን የፌዴራልና ክልል አመራሮች በሙሉ አክብሮታችንን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ በክልሉ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ አለመግባባቶችንና ቅራኔዎችን በሽምግልና ሥርዓት በማቀራረብና በመፍታት በክልሉ የተረጋጋ የፖለቲካ አውድ እንዲፈጠር እና ሕዝባችንም በሙሉ አቅሙ ትኩረቱን ወደ ልማት እንዲያዞር በሚደረገው ርብርብ ውስጥ የራሳችንን ዜግነታዊ ግዴታ ለመወጣት ብለን ስንነሳ፤ ይኽንኑ ቀና መሻታችንን ፊት በመንሳት በራቸውን በዘጉብን አመራሮች ደግሞ ማዘናችንን ኣንሸሽግም፡፡ የክልሉ መንግስት አመራሮች ውጤት ሊያስገኝ የሚያስችል ትብብር ለሰላማዊ የሽምግልና ባሕላችን ባለማሳየታቸው እና ጉዳዩን በሽምግልና ለመጨረስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፤ ከተደጋጋሚ ፍሬ አልባ ሙከራዎች በኋላ የጀመርነውን የሽምግልና እንቀስቃሴ ያቆምን መሆኑን ስንገልጽ እጅጉን በማዘን ጭምር ነው። መንግስት በማንኛውም ጊዜ ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት ፍላጎት በኖረው ጊዜ ሁሉ የሽምግልና ቡድኑ ሽምግልናውን ለመቀጠል ተባባሪ እንደሚሆንም አበክረን ለመግለጽ እንወዳለን። ሰላም ለሕዝባችን፥ ሰላም ለአገራችን! የማይነበብ ፊርማ ምንጭ_Belay Manaye

Source: Link to the Post

Leave a Reply