You are currently viewing #የክልል_እንሁን_ጥያቄዎች_ዘላቂ_ሰላምን_በሚያመጣ_መልኩ_ሊፈቱ_ይገባል! ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 04/2014 ዓ.ም                    አሻራ ሚዲያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ…

#የክልል_እንሁን_ጥያቄዎች_ዘላቂ_ሰላምን_በሚያመጣ_መልኩ_ሊፈቱ_ይገባል! ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 04/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ…

#የክልል_እንሁን_ጥያቄዎች_ዘላቂ_ሰላምን_በሚያመጣ_መልኩ_ሊፈቱ_ይገባል! ሰ.ሜሪካ :- ነሀሴ 04/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የተዋቀረችበት የ”ክልል” አደረጃጀት ኢትዮጵያውያን ልጆቿ ለሦስት ሺህ ዓመታት አብረው የኖሩበትን እንዲሁም በሰላምና በመቻቻል ተጋግዘው የመኖር እሴታቸውን ያጠፋና ሀገራችንን ለከፋ ችግር የዳረገ አወቃቀር መሆኑን እናት ፓርቲ በጽኑ ያምናል፡፡ ይህ የክልል አወቃቀር የአንድ ነጻ አውጪ ድርጅት በሆነው ሕገ መንግሥት ተደግፎ ሀገራችንን ለመበታተንና ከፋፍሎ ለመግዛት ብሎም በፕሮግራማቸው ያስቀመጡት ቀመረ ጊዜ ሲደርስ ሀገር ብለው ያቀዱትን ለመመሥረት ታስቦና ታቅዶ የተዘጋጀ እንጂ ያልተማከለ አስተዳደርን/ፌደራሊዝም/ ተግባራዊ ለማድረግና ራስን በራስ የማስተዳደርና መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በፍጥነት ለማኅበረሰቡ ለማድረስ ታስቦ ባለመሆኑ ሀገራችንን ለዘርፈ ብዙ ምስቅልቅል ችግር ዳርጓታል። መንግስት የሀገራችን መሠረታዊ ችግር የሆነው ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል ጨምሮ በጥናት ላይ የተመሠረተ ከቋንቋ በዘለለ ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ያልተማከለ አስተዳደርን ከማስፈን ይልቅ ከሕዝብ ጋር ግብ ግብ ውስጥ መግባትን ምርጫው በማድረጉ ምክንያት በብዙ ቦታዎች በተለይም በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ብዙ ወገኖቻችን የችግሩ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለበርካታ ዓመታት የታገሉለት ጥያቄ ኹሉንም ዜጋ በእኩልነት የሚያስተናግድና በሚናገሩት ቋንቋ፣ በሚከተሉት ሃይማኖት እና የፖለቲካ ዝንባሌ የማያገልል፣ ሀገር ያላትን በረከቶች በእኩልነትና ግልጽነት የሚያቋድስ፣ አንድነትን፣ እድገትንና ዘላቂ ሰላምን ለድርድር የማያቀርብ ሥርዓት እንዲዘረጋ እንጂ በየጊዜው ወደ እርስ በእርስ ግጭት የሚከትና ለአላስፈላጊ የሕይወት መሥዋዕትነትና ንብረት ውድመት የሚዳርግ ቀውስ ውስጥ ለመግባት አልነበረም። ሆኖም አኹን አኹን ዘላቂ መፍትሔን በሚያመጣ መልኩ እና ሕጋዊ መሠረትን የተከተለ ሳይሆን በግብታዊነት፣ ከግል ተነሳሽነትና ፍላጎት/Ego/ በመነጨ፣ በቅርርብ እና ለጊዜያዊ ፖለቲካ ትርፍ ብቻ ሲባል ለአንዱ የተሰጠው ችሮታ ለሌላው እየተነፈገ በሰላሙ የምናውቀው አካባቢ የብጥብጥ ማዕከል እየሆነ መጥቷል፡፡ የጉራጌን ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ ከሲዳማው እና ከደቡብ ምዕራቡ በምን እንደሚለይና እንደሚመሳሰል፣ የሕዝቡ ፍላጎት፣ የአስተዳደር አመችነትና መሰል ጥያቄዎችን እንዲሁም መርኆዎችን ሊመልስ በሚችል መልኩ ከሕዝቡ ጋር በመመካከርና በመግባባት ላይ ብቻ መፈታት ይገባዋል ብለን በጽኑ እናምናለን፡፡ ከዚህ በዘለለ ግን ጆሮ ዳባ ልበስ በሚል ከሕዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን በኃይል ለመፍታት የሚደረገው ሙከራ በየትኛውም የሕግ መስፈርት ተቀባይነት የለውም። ስለሆነም ፓርቲያችን የሀገራችንን ተጨባጭ ኹኔታና የሕዝባችንን ጥያቄ ግምት ውስጥ በማስገባት የሚከተሉትን የመፍትሔ ሀሳቦች ሊጠቁም ይወዳል። የሀገራችን አብዛኛው ችግር የሚመነጨው ከሕገ መንግሥቱ “የክልል አወቃቀር” ጋር በተያያዘ መሆኑ ታውቆ ከጊዜያዊ መፍትሔ ይልቅ ዘለቄታዊ መፍትሔና የችግሩ ምንጭ ላይ ያተኮረ አፋጣኝ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲጀመር እንጠይቃለን፡፡ በአኹኑ ሰዐት የክልልነት ጥያቄ እየጠየቁ ላሉ የማኅበረሰባችን ክፍሎች መንግሥት የኃይል አማራጭን ከመከተል ይልቅ ከሕዝባችን ጋር በቅርበት በመነጋገርና በመግባባት ብቻ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡ ሰላም ወዳድ የሆነው ሕዝባችን የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች እጅግ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ውጤት ላይ መድረስ እንጂ አላስፈላጊ መሥዋዕትነት ከሚያመጡ ድርጊቶች እንዲቆጠብ ፓርቲያችን ጥሪውን ያስተላልፋል። ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ እናት ፓርቲ ነሐሴ ፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply