የክርስቶስን መወለድ በአግባቡ ለማክበር ለሰው ልጆች ሕይወት፣ ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያንና ለእርሱ ቅዱስ ስፍራዎች ክብርን ስንሰጥ ነው አለች የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን።ቤተክርስቲያ…

የክርስቶስን መወለድ በአግባቡ ለማክበር ለሰው ልጆች ሕይወት፣ ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያንና ለእርሱ ቅዱስ ስፍራዎች ክብርን ስንሰጥ ነው አለች የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን።

ቤተክርስቲያኗ የክርስቶስ የልደት በአል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፋለች።

በመልዕክቷም ከራስ ወዳድነት መንፈስ እንውጣ በመላው አገራችን ሞት ይብቃ፣ ሰላም ይስፋፋ ብላለች።

የተራቡ፣ የተጠሙ፣ የታረዙ፣ የተበደሉ፣ የታመሙና የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን እናስታውስ ስትልም ገልጻለች።ከጎናቸው እንሁን እንርዳቸው እናጽናናቸው፡፡

ለኛ ምን ይደረግልን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ምን እናድርግ እንበል፤ መጠጊያ ለሌላቸው መሸሸጊያ እንሁንላቸው፡፡የሚገለሉ ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው እናድርግ፡፡ 

ዘመዳቸው እንሁን፡፡ ምክንያቱም የልደት በዓል ክርስቶስ ዘመዳችን እንደሆነ የሚያበሥረን በዓል ነውና፡፡ በልደት ምስጢር ማንም እንግዳ ሊሆን አይገባውም፡፡

የሰው ልጅ ለማኅበራዊ ችግሮቹ መፍትሔ ይፈልጋል፣ ሊፈልግም ይገባዋል፡፡

ነገር ግን ቆም ብሎ ከእርሱ የማሰብ ችሎታና አድማስ ባሻገር መመልከት ሲችል ብቻ ነው መፍትሔን የሚያገኘው በትህትና ወደ ምጡቁ አምላክ ሲመለከት ነው፡፡

ለፍትህ፣ ለእውነትና ለመልካም ነጻነት መሥራት የማንነቱ መሠረት መሆኑን የሚረዳው የልደት በዓልም ለፍትህ፣ ለእውነትና ለመልካም ነፃነት ሰውን የሚጠራ በዓል ነው፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 25 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply