የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተፈፀመ።

የቀብር ስነ ስርዓታቸው በቢሾፍቱ ከተማ ስታዲየም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የአስክሬን ሽኝት ተካሂዷል።

የክብር ዶክተር አርቲስት ለማ ጉያ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ92 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

አርቲስት ለማ ጉያ ላለፉት 65 ዓመታት ከ10 ሺህ በላይ ሥዕሎችን በፍየል ቆዳ ላይ በመሳል አድናቆትን ማትረፍ ችለዋል።

ሥራዎቻቸውንም በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ለማ ጉያ የሥነ-ጥበብ ማዕከል ውስጥ ለጎብኝዎች ያሳዩ ነበር።

የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ ባደረባቸው ሕመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም በ92 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

The post የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈፀመ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply