የክብር ዶ/ር ማሪቱ ለገሰ ከ23 ዓመት ቆይታ በኃላ በዛሬው ዕለት ወደ ሀገሯ ኢትዮጵያ ገብታለች፡፡የአንባሰሏ ንግስት በመባል የምትታወቀው የክብር ዶ/ር ማሪቱ ለገሰ ከ23 ዓመት የአሜሪካ ቆይ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/VrDXgWoX4Yc3hWXZFVvJ6MarkEOFkooInGv3K__V_8alw2zmRbKYb4VMdo9FSj4qVjGRphfAyFmKGu7ejp7sSSk5op13ZpkuOTqzJOIO3dezszrf1RLSuO5KPCiy_RlpnLk2fqZTEXqXNeCaeY2e4_68faMXDeRPL7qvVK_vzPbz4ZvtWLEbrTbam3i3nqqy8ZPRiwe_G_fG1gq5jhrU_G3xFNTO0UD30DA9Yn4cndj7rLp6iuClRq6yvcsE7YXfnWqUV9wKya0w7Zr0zMeQRM9PHLBFQrlAsm7eBoN66YdEfS5-k3ZJt1WFVik2ivLGH5lQaGS_ikGJ8-8WX2mvfg.jpg

የክብር ዶ/ር ማሪቱ ለገሰ ከ23 ዓመት ቆይታ በኃላ በዛሬው ዕለት ወደ ሀገሯ ኢትዮጵያ ገብታለች፡፡

የአንባሰሏ ንግስት በመባል የምትታወቀው የክብር ዶ/ር ማሪቱ ለገሰ ከ23 ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኃላ ዛሬ ታሕሳስ 24/2015 ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳለች።

ዝነኛዋ ድምፃዊት ማሪቱ ለገስ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስም በቤተሰቦቿ፣በሙያ አጋሮቿ እንዲሁም በአድናቂዎቿ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።

ከአሜሪካ ሽኝት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው ማሪቱ ለገስ፤ በኢትዮጵያ ቆይታዋ አዲስ አልበሟን ለአድማጭ የምታቀርብ ሲሆን፤ አዲስ አበባን ጨምሮ ደሴ እና በተለያዩ ከተሞች የሙዚቃ ሥራዋን እንደምታቀርብም ተነግሯል።

የወሎ ዩኒቨርስቲ ከ7 ዓመት በፊት ያበረከተላትን የክብር ዶክትሬት ለአርቲስቷ በአካል እንደሚያበረክትም ታውቋል።

ዝነኛዋ ድምፃዊት ማሪቱ ለገሰ ታሕሳስ 29/2015 የመጀመሪያ ኮንሰርቷን በደሴ ከተማ እንደምታቀርብም ተነግሯል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply