የኮሌራ ወረርሺኝ ለክልሉ አሁንም ስጋት ነዉ ሲል የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡ከተቀሰቀሰ 18 ወራት የሆነዉ የኮሌራ ወረርሺኝ አሁንም ለክልሉ ስጋት መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ለኢት…

የኮሌራ ወረርሺኝ ለክልሉ አሁንም ስጋት ነዉ ሲል የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡

ከተቀሰቀሰ 18 ወራት የሆነዉ የኮሌራ ወረርሺኝ አሁንም ለክልሉ ስጋት መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግሯል፡፡

በዚህ 18 ወራትም 11ሺህ 6መቶ ሰዎች በወረርሺኙ ተጠቅተዋል፡፡

በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ቁጥጥር እና አደጋ ምላሽ ሰጪ እንዲሁም የላቦራቶሪ አገልግሎት አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ ከበበዉ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ወረርሺኙ በባሌ አከባቢ ተነስቶ ወደ 11 ዞኖች እና 5 ከተማ አስተዳድሮች መስፋፋቱን ገልጸዋል፡፡

አስተባባሪዉ እንደነገሩን ወረርሺኙን ወደ 6ዞኖች እና 3 ከተማ አስተዳድሮች ላይ መቆጣጠር ተችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በ5 ዞኖች እና በ 2 ከተማ አስተዳድሮች ላይ እንደሚገኝ ነግረዉናል፡፡

ወረርሺኙ የለም ለማለት ለተከታታይ አርባ ቀናት ዜሮ ኬዝ ሪፖርት መደረግ አለበት ያሉ ሲሆን፤አሁን ላይ ችግሩ አለባቸዉ ከተባሉ ዞኖች እና ከተማ አስተዳድሮችም የለባቸዉም የሚል ሪፖርት የምንጠብቅባቸዉ ቦታዎች አሉ ነዉ ያሉት፡፡

ባለፉት 18 ወራት በክልሉ ወደ 11ሺህ6መቶ የሚሆኑ ሰዎች በወረርሺኙ ተይዘዉ እንደነበርም አስተባባሪዉ ነግረዉናል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት አገላለጽ ከ100 ሰዉ አንድ ሰዉ እና ከዛ በታች ከሞተ የሞት ምጣኔዉ ተቀባይነት ያለዉ ነዉ ይባላል ያሉት አስተባባሪዉ በክልሉ በወረርሺኙ ምክንያት የተከሰተዉ የሞት ምጣኔም ተቀባይነት ያለዉ ነዉ ብለዉናል፡፡

ለክልሉ ወደ 3 ሚሊየን ዶዝ ክትባት መሰጠቱን የገለጹት ዶ/ር ተስፋዬ ፤ ክትባቱ በተሰጠባቸዉ ቦታዎችም ወረርሺኙን መቆጣጠር መቻሉን ነግረዉናል፡፡

አሁን ላይ ወረርሺኙ በምዕራብ ሃረርጌ፣በምስራቅ ሃረርጌ፣ በምዕራብ ባሌ ፣ በምስራቅ ባሌ እና ባሌ እንዲሁም በማያ እና ሻሸመኔ ከተማ አስተዳድሮች ዉስጥ ይገኛል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply