የኮሎምቢያ ባሕር ኃይል 100 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ኮኬይን ያዘ

https://gdb.voanews.com/01000000-0aff-0242-14c9-08dbb5402272_w800_h450.jpg

የኮሎምቢያ ባሕር ኃይል፣ ሦስት ቶን የሚመዝንና ቢያንስ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ኮኬይን መያዙን አስታውቋል።

በከፍተኛ ፍጥነት ለማምለጥ ከሞከረው መርከብ ላይ የተያዘው አደንዛዥ ዕፁ፣ ወደ ማዕከላዊ አሜሪካ እየተጓጓዘ እንደነበር ተነግሯል።

አራት የመርከቡ ሠራተኞችም በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ፣ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል። አደንዛዥ ዕፅ በማምረትና በሕገ ወጥ መንገድ በማጓጓዝ ተጠርጥረው ምርመራ ይደረግባቸዋል፤ ሲሉ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ኮሎምቢያ፣ በዓለም ከፍተኛ የኮኬይንና አነቃቂው ቅመም የሚገኝበት የኮካ ቅጠል አምራች ሀገራት አንዷ እንደኾነች፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply