የኮምቦልቻ እፅዋት ክሊኒክ ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ንብረቶቹ እንደወደሙበት አስታወቀ

ለአፋር ክልልና በምስራቃዊ አማራ ለሚገኙ ዞኖች የሰብል ተባይና በሽታ መከላከል አገልግሎት ይሰጥ የነበረው የኮምቦልቻ እጽዋት ክሊኒክ ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ንብረቶቹ በህወሓት ኃይሎች መዘረፋቸውንና እንዲውድሙ መደረጋቸውን አስታወቀ፡፡

ክሊኒኩ ላይ የደረሰው ዘረፋና ውድመት በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት እየተከሰተ ያለውን የበርሃ አምበጣ ለመከላከል አዳጋች ያደርገዋል ሲሉ የክሊኒኩ ኃላፊ መሐመድ ይመር ገልጸዋል፡፡

የፌደራሉ ግብርና ሚኒስትር የእርሻና እጽዋት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር መለስ መኮነን በጦርነቱ ምክንያት የተዘረፉና ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት ለማቋቋም እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

የበረሃ አምበጣ በአሁኑ ሰዓት ሥጋት ባይሆንም ከተከሰተ ግን ለመከላከል የሚያስችል አቋም ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply