የኮሮና ቫይረስን በመከላከል ረገድ የወጣውን ፕሮቶኮል ማሟላት ለቻሉ 11 ሆቴሎች እውቅና መስጠቱን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃትና ለመደገፍ የአሰራር ፕሮቶኮል አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡በሆቴሎችና አገልግሎት መስጫ ተቋማት የወጣው ፕሮቶኮል ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ላይም የኬሚካል ርጭት ተካሂዷል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ጌታቸው ለአሐዱ እንደተናገሩት የወጣው ፕሮቶኮል ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም፡፡ነገር ግን በአንዳንድ ሆቴሎች እና በአገልግሎት መስጫ ተቋማት በከፊል ተግባራዊ ሲደረግ ይስተዋላል ብለዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፕሮቶኮሉን ሙሉ በሙሉ ሲተገብሩ ላገኛቸው ለ11 ሆቴሎች እውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡ሌሎች ሆቴሎችም የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የወጣውን የፕሮቶኮል መመሪያ አሟልተው ሲገኙ እውቅና እንደሚሰጣቸው አቶ አለማየሁ ተናግረዋል በዚህም ክልሎችን የመደገፍ ስራ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በተለይም የሀገር ውስጥ የጎብኚዎች እንቅስቃሴ አለ የሚባል ቢሆንም ጥንቃቄ ከማድረግ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ክፍተቶች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡የውጪ ሀገራት ጎብኚዎች ከጉዞ እገዳው ጋር በተያያዘ ያለው እንቅስቃሴ የተገደበ መሆኑንን ተናገሩት አቶ አለማየሁ በገቢ ላይም ተጽዕኖ እንዳሳደረም ገልጸዋል፡፡

ቀን 26/06/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply