የኮቪድ 19 መከላከያዎችን አለመተግበር በመንግስት ባለስልጣናት ጭምር መስተዋሉ እንዳሳሰበዉ የጤና ሚንስቴር አስታወቀ፡፡ሚንስቴሩ እንዳለዉ የመንግስት ባለስልጣናትና ተወካዮች የኮቪድ 19 መከላ…

https://cdn4.telesco.pe/file/COWXD7ndmenK-nLcI-FLzNrCNg3hr_KkRxDVHw_bxqtvjHW-6D13P8G9QEG3o-8XdHodjZLPIPEDOc0WTNVZlpxI5fT2JLS-0su_ne-qppjO-ZH4MHEUBoQq-v9rKTYSlL0G4IMqJR418Vp-J2RojCrLcGlvv7Pid1TGzHPGI1cq-F7W6iattNUrJmbaz67jzCrXYl93viU5-kapAiOO0HF8gbpwuCpyUMA9UWVKAV3o6QRy_cp4nEs15oenLkFLwKHHYzNGpBEqcSuuwJNOseHsh35kH57x_Jf9nPI3uT2ZE2CJMhtII950pmoLl-vDaptsWhWEDdK3U_QgEGeBsQ.jpg

የኮቪድ 19 መከላከያዎችን አለመተግበር በመንግስት ባለስልጣናት ጭምር መስተዋሉ እንዳሳሰበዉ የጤና ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

ሚንስቴሩ እንዳለዉ የመንግስት ባለስልጣናትና ተወካዮች የኮቪድ 19 መከላከያዎችን አለማድረጋቸው ትልቅ ስጋትን ፈጥሮብኛል ብሏል፡፡
የመንግስት ባለስልጣናትና ተወካዮች በትላልቅ መድረኮች ላይ ሳይቀር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ወይም ማስክ ሳይጠቀሙና ርቀትን ሳይጠብቁ መቀመጣቸው ለህብረተሰቡ የተሳሳተ መልዕክት እያስተላለፈ ይገኛል ነዉ ያለዉ፡፡

ይህም እስካሁን ባለው የኮቪድ 19 መከላከል ስራ አንዱ ችግር ሆኖ መቀጠሉም ሚንስቴሩ አስታዉቋል፡፡
በጥር ወር የጭምብል ባንክ ወይም ማስክ ማሰባሰብ እንደሚከናወንና
ማስክ የመግዛት አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ማስክ የመግዛት ሂደት እንደሚኖርም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

የጤና ሚንስቴር ከሰሞኑ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ የኮቪድ 19 በመከላከል ዙሪያ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መዘናጋት መኖሩንና ወደ ጽኑ ህሙማን ማዕከል የሚገቡ የቫይረሱ ተጠቂዎችም ቁጥራቸዉ በየጊዜዉ እየቸመረ መምጣቱን አስታዉቋል፡፡
ይህ መዘናጋት የከፋ ዋጋ እንዳያስከፍልም ህብረተሰቡ የጥንቃቄ መመሪያዎችን በአግባቡ እንዲተገብር ሚንስቴሩ አሳስቧል፡፡

በመቅደላዊት ደረጀ
ታህሳስ 30 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply