የኮቪድ-19 የፅኑ ህክምና ታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም እንደ አገር የፅኑ ህክምና መርጃ መሳሪያዎች ዕጥረት እንዳለ የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አስታወቀ፡፡

በኢንስትቲዩቱ የኮቪድ-19 የህክምና ተቋማት አስተባባሪ አቶ ሔኖክ ሃይሉ ለአሀዱ እንደገለፁት በኢትዮጵያ ምልክት ሳያሳዩ በኮቪድ-19 የሚጠቁ ዜጎች ቁጥር ጨምሯል፤ በተመሳሳይ በቫይረሱ እና በተያያዥ ህመሞች ምክንያት ወደ ፅኑ ህክምና የሚገቡ ታካሚዎች ቁጥርም ጨምሯል ብለዋል፡፡

ምንም እንኳን ወደ ፅኑ ህክምና ክፍል የሚገቡ ታካሚዎች ቁጥር ቢጨምርም በአገር አቀፍ ደረጃ የፅኑ ህክምና መርጃ መሳሪያዎች ዕጥረት እንዳለ ኢንስትቲዩቱ አስታውቋ፡፡በአዲስ አበባ በመንግስት የጤና ተቋማት ያሉ ለመተንፈስ የሚረዱ መሳሪያዎች በቁጥር 45 ብቻ መሆናቸውን ያስታወቁት አቶ ሔኖክ በቅርቡ ተጨማሪ 50 መሳሪያዎች ይገባሉ ብለዋል፡፡ይህም ሆኖ ዕጥረቱ እንደማይቀረፍ ያስታወቁት የኢንስትቲዩቱ ባለሙያ መፍትኤው በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታየው ቸልተኝነት ተቀርፎ ጥንቃቄ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

******************************************************************************

ቀን 14/ 03/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply