የኮንሰርት ፕሮግራም የቀን ለውጥ በማድረግ ለግንቦት 6 እና 7 ቀን 2014 ዓ.ም መተላለፉን ስለመግፅ ========================= ባህርዳር:- ሚያዚያ 23/2014 ዓ.ም…

የኮንሰርት ፕሮግራም የቀን ለውጥ በማድረግ ለግንቦት 6 እና 7 ቀን 2014 ዓ.ም መተላለፉን ስለመግፅ ========================= ባህርዳር:- ሚያዚያ 23/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ከአሁን በፊት ለአማራ ፋኖ በወሎ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ለሚያዚያ 29 እና ሚያዚያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት የቀን ለውጥ በማድረግ እንዲራዘም ተደርጓል። የአማራ ህዝብ ከውስጥ በባንዶችና ከውጭ ጠላቶች በገጠመው የህልውና ትግል በሁሉም አቅጣጫዎች ጦርነት ተከፍቶበት ይገኛል።በዚህ መሰረትም የአማራ ፋኖ ለአማራ ህዝብ ህልውና መከበርና እንደ ሀገር ኢትዮጵያን ለማስከበር በየግንባሩ መስዋእትነት እየከፈለ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት ለፋኖ ድጋፍ የሚሆን የኮንሰርት ፕሮግራም አዘጋጅቶ የቀጠሮ ሰአቱን እየጠበቀ ቢሆንም በህዝባችን ላይ በተፈጠረው ችግር የፕሮግራሙን ቀን ለመቀየር ተገደናል።ስለሆነም የአማራ ፋኖ በወሎ ሚያዚያ 29 እና 30 በደሴ ከተማ ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት መኖሩን ቀደም ብልን የገለፅን መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ሰሞኑን በህዝባችን ላይ በተፈጠረው ችግር እንደ አማራ የተሰማን ሀዘን ጥልቅ መሆኑን እየገለፅን የህዝባችን ስሜትና ችግር የእኛ ችገርና ስሜት መሆኑን አውቀን የታሰበው ፕሮግራም ለግንቦት 7ና 8 ያስተላለፍን መሆኑን እንገልፃለን። የአማራ ፋኖ በወሎ ኑ ፋኖን እንደግፍ እያለ ግንቦት 6ና 7 ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጅቶ ከ4 ወር በላይ የሰለጠኑ የፋኖ ሰራዊትን ለማስመረቅ ዝግጅቱን አጠናቆ ይጠብቅዎታል። ማለትም ግንቦት 6 ከጧቱ 2:00 ሰአት ጀምሮ በታላቁ የሆጤ ስታድየም ሰልጣኞችን ያስመርቃል።በእለቱ ከ8:00 ሰአት ጀምሮ በታላቁ ቤተመንግሥት መርሆ ግቢ ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት በማዘጋጀት ኑ ፋኖን እንደግፍ ይለናል!!! ይህ የምረቃና የኮንሰርት ፕሮግራም ለየት የሚያደርገው ለአማራ ህዝብ ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ያሉ ስመ ገናና ታጋዮች እና ታዋቂ ግለሰቦች ይገኙበታል። እንድሁም የአማራ ህዝብ አለኝታ የኢትዮጵያ መከታ የሆነው የአማራ ፋኖ የትግል መዝሙር ስለሚመረቅ ዝግጅቱን በአይነቱ ልዩ ያደርገዋል። ገቢው በትግሉ ለተሰዉ የትግሉ ሰማዕታት ቤተሰቦችና ለቆሰሉ ጓዶች ድጋፍ የሚውል ሲሆን ተወዳጅ አርቲስቶች መድረኩን ያደምቁታል። #አዘጋጅ:-የአማራ_ፋኖ_በወሎ #ደሴ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply