የኮንስትራክሽን ሳይት ላይ በደረሰ አደጋ የሰው ህይወት አለፈ፡፡

ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ13 አያት ሪል እስቴት በሚያስገነባዉ የቤት ግንባታ ላይ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርት ተንዶ ዕድሜዉ ሀያ ዓመት የሆነ የድርጅቱ ሰራተኛ ወዲያዉ ህይወቱ አልፏአል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የወጣቱን አስከሬን ከፍርስራሽ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ ማስረከባቸውን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን የስራ ላይ አደጋ በአንድ ወር ዉስጥ የዛሬዉን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply