የኮንሶና የአሌ ጎሳን በማጋጨት የተጠረጠሩ ታሠሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የኮንሶና የአሌ…

የኮንሶና የአሌ ጎሳን በማጋጨት የተጠረጠሩ ታሠሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የኮንሶና የአሌ ማኅበረሰብ አባላትን አጋጭተዋል፣ የሰዉ ሕይወትና ንብረት አጥፍተዋል ብሎ የጠረጠራቸዉን 310 ሰዎች አሰረ። የቢሮው ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዴ ለዶቼ ቬለ (DW) እንዳሉት ቢሮው ሰሞኑን ባካሄደው ዘመቻ ካሰራቸዉ ተጠርጣሪዎች ዉስጥ ባለ ሥልጣናት፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ገበሬዎች ይገኙበታል። ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሁለቱ ማህበረሰብ አባላት መካከል ደም ሲያፋስስ የቆየው ግጭት ባለፈው እሁድ ባህላዊ የእርቅ ስረዓት ከተደረገ በኋላ የአካባቢው ሰላም እየተሻሻለ ነዉ። ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የኮንሶና የአሌ ብሄር ባህላዊ ንጉሦችና የአገር ሽማግሌዎች «ከእርቅ ስረዓቱ በኋላ የንግድ ተቋማት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፣ ለወራት ተቋርጠው የከረሙ ገበያዎችም መቆም ጀምረዋል» ብለዋል ሲል ካፒታል ኒውስ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply