You are currently viewing የኮንዶሚንዬም እጣ የወጣበት መተግበሪያ በገለልተኛ አካል እንዲመረመር ሲል ኢሰመጉ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ሀምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ  የኮንደሚ…

የኮንዶሚንዬም እጣ የወጣበት መተግበሪያ በገለልተኛ አካል እንዲመረመር ሲል ኢሰመጉ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኮንደሚ…

የኮንዶሚንዬም እጣ የወጣበት መተግበሪያ በገለልተኛ አካል እንዲመረመር ሲል ኢሰመጉ አሳሰበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኮንደሚንየም እጣ መጭበርበርን በተመለከተ ለተነሳው ቅሬታ እጣው የወጣበት መተግበሪያ በገለልተኛ አካል እንዲመረመር እና ውጤቱ ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳስቧል። በከተማ አስተዳደሩ የሚገነቡ መኖሪያ ቤቶች ግልፀኝነትንና ፍትሃዊነትን በተከተለ ሁኔታ ለማህበረሰቡ እንዲደርሱ ማድረግ አለበት ሲል አሳስቧል። በጥቅሉ ኢሰመጉ የሚከተሉትን 6 መልዕክቶች አስተላልፏል:_ 1) የእጣ ማውጫው መተግበሪያ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የበለጸገ መሆኑን፣ የፌደራልን ጨምሮ ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ይሁንታን ያገኘና በግል ተቋማት ታዛቢዎች ጭምር ታይቶ እንደተረጋገጠ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገልጾ አንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ መጭበርበር የተፈጠረ ሲሆን መንግስት ከዚህ በቂ ትምህርት በመውሰድ ቴክኖሎጂን አስመልክቶ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣ 2) መንግስት ዕጣ ለማውጣት ተጠቅሜበታለው ያለውን ሶፍትዋር መተግበርያ በገለልተኛ አካል እንዲያስመረምር እንዲሁም ለህዝብ ውጤቱን ይፋ እንዲያደርግ ፣ 3) በጉዳዩ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦችና አመራሮች ላይ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግ፣ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለሚገባቸው ሰዎች በአግባቡ እንዲያስተላልፍ እንዲሁም የዜጎችን በቂ የሆነ የኑሮ ደረጃ የመኖር መብትን እንዲያረጋግጥ፣ 4) በ4ኛ ዙር ያልተካተቱትን የ20/8ዐ የባለ ሶስት መኝታ ቤት እድለኞችን መንግስት በአፋጣኝ ግልጽና ተአማኒ በሆነ መንገድ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ 5) ለኢሰመጉ እየደረሱ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በተለያዩ ቦታዎች ከተከራዮች ተመላሽ የተደረጉ የመንግስት ቤቶች ያለአገልግሎት ታሽገው የተቀመጡ በመሆኑ ወደ አገልግሎት በማስገባት የነዋሪውን የቤት ችግር አስተዳደሩ እንዲፈታ፣ 6) የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት፣ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ጥፋተኛ ሆነው የተገኙትን በህግ ተጠያቂ በማድረግ መንግስት ያለበትን ሀላፊነት እንዲወጣ ኢሰመጉ ጥሪውን ያቀርባል ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply