የኮንጎ እና ዩንጋንዳ ጥምረት ጦር የአማጽያንን ይዞታዎች ደመሰስን አለ

የኮንጎ ዴሞክራቲኮ ሪፐብሊክ እና የዩናጋዳ ሠራዊት ጥምረት በኮንጎ ምስራቃዊ ግዛት ውስጥ የሚገኙ አማጽያንን ጠንካራ ይዞታዎች መደምሰሳቸውንና 35 አማጽያንን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ትናንት ባወጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ከሁለቱ አገሮች የተውጣጣው ጦር “በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሰሜን ኩቩ እና ኢቱሪ ክፍለ ግዛት ውስጥ የሚገኙ አዳዲስ የጠላት ሰፈሮችን” ማጥቃታቸውን የኮንጎ ጦር ሠራዊት ባወጣው የትዊት መልዕክት አስታውቋል፡፡

እኤአ ህዳር 30 የሁለቱ አገሮች ጥምረት ጦር እምርጃ መውሰደ ከጀመረ ወዲህ፣ ብዙ ሰላማዊ ሰዎች ላይ በዩጋንዳና ኮንጎ ውስጥ ለደረሰው የሽብር እልቂት ተጠያቂ የሆነውን የተባበሩት ዴሞክራቲክ ኃይሎች ወይም ኢ.ዲ.ኤፍ እየተባለ የሚጠራውን የአማጽያን ቡድን መደምሰሱን አስታውቋል፡፡ 

ኢ.ዲ.ኤፍ በዩጋንዳና ኮንጎ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ለደረሱ የቦምብ ፍንዳታዎች ተጠያቂ የተደረገ ድርጅት መሆኑም ተመልክቷል፡፡  የኢ.ዲ.ኤፍ ቡድን አባላት በአብዛኛው የዩንጋዳውን መሪ ፕሬዚዲንት ሙሲቪኒ መንግስት የሚቃወሙ ሙስሊሞች ሲሆኑ፣ እኤአ በ1995 በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ የተመሰረቱ መሆኑ ተነገሯል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply