
የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ህብረት ከአቡነ ማትያስ ውጪ እውቅና የምሰጠው ፓትርያርክ የለም አለ። ጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ስም የተደረገውን ህገ ወጥ ሹመት እንደማይቀበል አስታውቋል። መግለጫውን ተከትለው የኮፕቲክ ቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የቤተክርስትያኗ የለንደን ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አንባ አንጄላዎስ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ኃሳብ “የኦርቶዶክስ እምነትን ጠብቆ ለማቆየት የሐዋርያት መተካካት የቤተ ክርስቲያኗን ቀኖናዊ ህጋዊነትና የክህነት አግባብ ማስቀጠያ ዋነኛው መንገድ ሆኖ ቆይቷል” ብለዋል። ከህብረቱ በወጣው መግለጫ “በአቡነ ሳዊሮስ የተመራው የ26 ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት የቤተ ክርስቲያንን ህግ የጣሰ ነው” ያሉት ሊቀ ጳጳስ አንባ ቶማስ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር በተያያዘ ግንኙነት የሚኖራቸው ከአቡነ ማትያስ ጋር ብቻ መሆኑን ገልፀዋል። የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ህብረት ሊቀ ጳጳስ በመግለጫቸው ከቤተ ክርስትያኗ ስርዓት ውጪ የተፈፀመው ሹመት የተወገዘ መሆኑን አስታውቀው የኮፕቲክ ኦሮቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ህብረት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጎን መሆኗን እናሳውቃለን ስለማለቱ አዲስ ዘይቤ ነው የዘገበው። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post