You are currently viewing የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ህብረት ከአቡነ ማትያስ ውጪ እውቅና የምሰጠው ፓትርያርክ የለም አለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 23 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲ…

የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ህብረት ከአቡነ ማትያስ ውጪ እውቅና የምሰጠው ፓትርያርክ የለም አለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 23 ቀን 2015 ዓ/ም አዲ…

የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ህብረት ከአቡነ ማትያስ ውጪ እውቅና የምሰጠው ፓትርያርክ የለም አለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 23 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ስም የተደረገውን ህገ ወጥ ሹመት እንደማይቀበል አስታውቋል። መግለጫውን ተከትለው የኮፕቲክ ቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የቤተክርስትያኗ የለንደን ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አንባ አንጄላዎስ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ኃሳብ “የኦርቶዶክስ እምነትን ጠብቆ ለማቆየት የሐዋርያት መተካካት የቤተ ክርስቲያኗን ቀኖናዊ ህጋዊነትና የክህነት አግባብ ማስቀጠያ ዋነኛው መንገድ ሆኖ ቆይቷል” ብለዋል። ከህብረቱ በወጣው መግለጫ “በአቡነ ሳዊሮስ የተመራው የ26 ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት የቤተ ክርስቲያንን ህግ የጣሰ ነው” ያሉት ሊቀ ጳጳስ አንባ ቶማስ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር በተያያዘ ግንኙነት የሚኖራቸው ከአቡነ ማትያስ ጋር ብቻ መሆኑን ገልፀዋል። የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ህብረት ሊቀ ጳጳስ በመግለጫቸው ከቤተ ክርስትያኗ ስርዓት ውጪ የተፈፀመው ሹመት የተወገዘ መሆኑን አስታውቀው የኮፕቲክ ኦሮቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት ህብረት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጎን መሆኗን እናሳውቃለን ስለማለቱ አዲስ ዘይቤ ነው የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply