የወላይታ ሶዶ ተመራቂ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ቅሬታ እያቀረቡ ነው፡፡

በወላይታ ሶዶ ዮኒቨርሲቲ የሚማሩ የ2016 ተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ ጊዜያችን ያለ አግባብ ተራዝሞብናል በማለት ቅሬታቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡

ተመራቂ ተማሮዎቹም ጥያቄያችን መልስ ያግኝ በሚል ትምህርት ማቆም አድማ እንዳደርጉ ለኢትዮ ኤፍ ኤምቅሬታቸውን አሰምተዋል ሰተዋል፡፡
ተማሪዎቹ በ2016 መመረቅ ሲግባን 2017 መጨረሻ ወር ላይ ትመረቃላችሁ እየተባልን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ያሉ ተመራቂ ተማሪዎች በዚህ ዓመት ቢመረቁም እኛ ግን እንድ አመት እንዲጨመርብን ተደርገናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህ ጉዳይ እኛ ተማሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ወላጆቻችን ላይም ጫና የሚያሳድር በምሆኑ ከወዲሁ ችግሩ ይቀረፍልን ብለዋል፡፡

ለመመረቅም 3 ሴሚስተር እንደሚቀራቸው ነው ተማሪዎቹ ያነሱት፡፡
ጣቢያችንም ጉዳዩን ለማጣራት የዮኒቨርስቲው ዓመራሮችን በተደጋጋሚ ቢያነጋግርም ፍቃደኛ አልሆኑም።

በሐመረ ፍሬው

ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply