የወልቂጤ ሆስፒታል የግንባታ ሂደት 60 በመቶ መድረሱ ተገለጸ

የወልቂጤ ሆስፒታል የግንባታ ሂደት 60 በመቶ መድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በ600 ሚሊየን ብር ወጪ በጉራጌ ዞን እየተገነባ ያለውን የወልቂጤ ሆስፒታል የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ መንግሥት በጀት እየተገነባ ያለው ሆስፒታል ለቀቤና ፥ ለአበሽጌ ወረዳ እና ለወልቂጤ ከተማ ህዝብ ከፍተኛ አገልግሎት ይሰጣል በሚል እንደተገነባ ተናግረዋል ፡፡

የሆስፒታሉ መገንባት የህብረተሰቡን የጤና ተደራሽነት ለማሳደግ ፋይዳው የጎላ መሆኑ መገለጹን የክልሉ መንግስት አስታውዋል።

የወልቂጤ ሆስፒታል የግንባታ ሂደት 60 በመቶ መድረሱ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የወልቂጤ ሆስፒታል የግንባታ ሂደት 60 በመቶ መድረሱ ተገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply