የወልቂጤ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመረቁ

የወልቂጤ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያምሰረቋቸውን ተማሪዎች አስመረቁ፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 472 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይም የመቅደላ ዓምባ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 824 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ በዛሬው ዕለት በዋናው ግቢ በተፈጥሮ ሳይንስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች የሰለጠኑ 480 ተማሪዎች የተመረቁ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በነገው እለት ይመረቃሉ፡፡

በምረቃ መርሀ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገርና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

መረጃው የደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን እና የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ነው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የወልቂጤ እና መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመረቁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply