የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ከሃዲው የትህነግ ቡድን መደምሰሱን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ነው

የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ከሃዲው የትህነግ ቡድን መደምሰሱን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ከሃዲው የትህነግ ቡድን መደምሰሱን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡
ነዋሪዎቹ ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡
በዚህ ወቅት የከተማው ነዋሪዎች አማራ በመሆናችን ብቻ ለ30 ዓመታት ሲደርስብን የነበረው ግፍ በማብቃቱ ነፃነታችንን በአደባባይ ለመግለፅ በቅተናል ብለዋል፡፡
ህዝቡ ለሰሜን እዝ አምስተኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ያለውን ፍቅርም እየገለፀ እንደሚገኝ አብመድ ዘግቧል፡፡

The post የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ዳንሻ ከተማ ነዋሪዎች ከሃዲው የትህነግ ቡድን መደምሰሱን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply