የወልቃይት ወረዳ የሚሊሻ አባላት ወደ ተሰጣቸው የግዳጅ ቀጠና ሽኝት ተደርጎላቸዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የወልቃይት ወረዳ…

የወልቃይት ወረዳ የሚሊሻ አባላት ወደ ተሰጣቸው የግዳጅ ቀጠና ሽኝት ተደርጎላቸዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የወልቃይት ወረዳ የሚሊሻ አባላት ወደ ተሰጣቸው የግዳጅ ቀጠና ሽኝት ተደርጎላቸዋል። በሽኝት መርሀግብር የተገኙት የወልቃይት ወረዳ አስተዳደር አቶ ክብረአብ ስማቸው ለዘማች ሰራዊቱ መልእክት አስተላልፈዋል። “እኛ ታሪካችን በደም እየጻፍን የመጣን በመስዋዕትነት የሀገር ዳር ድንበር ያስከበርን ኩሩ ኢትዮጵዊያን፣ በአማራነታችን የማንደራደር ነን፣ አሁንም የሀገር አንድነትን ለመበተን የተነሱ አካላትን እስከ መጨረሻ እንታገላቸዋለን ድል ለኢትዮጵያ” ብለዋል። የወልቃይት ወረዳ ምሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ዓባይ ማማይ በበኩላቸው ሰራዊቱ በተሰጣቸው የግዳጅ ቀጠና በወኔ እና እና በቁርጠኝነት እንዲዋጡ ጥሪያቸውን ስለማስተላለፋቸው የወልቃይት ወረዳ አስተዳደር አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply