የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወጣቶች በባህርዳር ከተማ ውይይት አደረጉ!! ባህርዳር :- የካቲት 15/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በዛሬው እለት ከ300 በላይ የሚ…

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ወጣቶች በባህርዳር ከተማ ውይይት አደረጉ!! ባህርዳር :- የካቲት 15/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በዛሬው እለት ከ300 በላይ የሚሆኑ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ወጣቶች መላው የአማራ ክልል ከተሞችንና ዞኖችን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ባህርዳር ከተማ ገብተዋል። የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ከ2008 በፊት በጉልበት የአማራን ባህል ፣እምነትና ቋንቋ ባላገናዘበ መልኩ በወቅቱ በነበረው ስርዓት በኃይል በመጫን እና በማስገደድ የወልቃይት ሴቲት ሁመራ ዞንን ከወንድሙ የአማራ ህዝብ ተነጥሎ እንዲቆይ ተገዶ ነበር ብለዋል። ይህ ትግል ሲጀምር ሁሉም ከዳር እስከ ዳር የተነሳ ቢሆንም ባህርዳር ላይ “ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ!” በማለት ከእናንተ ጎን በመቆም እስከ ህይወት መሰዋእትነት የተከፈለ መሆኑ ይታወሳል። በትግላችንም ትልቅ ድልን ተጎናጽፈናል። የባህርዳር ከተማ ወጣቶች ለወንድም የወልቃይት ህዝብን ነፃ ለማውጣት ከ56 ወጣቶች በላይ ህይወታቸውን ገብረዋል።የጀመርነውን ትግል በህጋዊ መንገድ ፍጻሜ ለማድረስ በጋራ የሚከፈለውን ለመክፈል ከጎናችሁ ነን ሲሉ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተ/ም/ከንቲባ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ተናግረዋል ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply