You are currently viewing የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አደረጉ!! ባህርዳር:-የካቲት 16/2014 ዓ.ም፣                 አሻራ ሚዲያ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ…

የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አደረጉ!! ባህርዳር:-የካቲት 16/2014 ዓ.ም፣ አሻራ ሚዲያ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ…

የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አደረጉ!! ባህርዳር:-የካቲት 16/2014 ዓ.ም፣ አሻራ ሚዲያ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የእንጅባራ ከተማ ከንቲባ እና ሌሎች አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የአገው ፈረሰኞች ማኅበር እና የእንጅባራ ከተማ ወጣቶች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) ወጣቶችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የዩኒቨርሲቲውን አጭር ታሪክ አስተዋውቀዋል። ይህ የወጣቶች ጉዞ በጎንደር እና በባህርዳር የተካሄደ ሲሆን ህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የማጠናከር ዓላማ እንዳለውም ተገልጿል። የአማራ ክልል የብልፅግና ሊግ ወጣቶች ኃላፊ አቶ ጋሻው ተቀባ እንደገለፁት የጉዞው ዓላማ የወልቃይት ጠገዴ ወጣቶች የአማራ ባህል፣ ታሪክ እና ወግ እንዲያውቁ ማድረግ ሲሆን ከሌሎች የአማራ ህዝቦች ጋር ያለውንን ወነድማዊ ትስስር ማጥበቅም ሌላኛው ዓላማ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ አቶ ጋሻው አያያይዘው እንደገለፁት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ማንነቱን ተቀምቶ በአምባገነኑ ትህነግ ሲተዳደር እንደቆየና በእልህ አስጨራሽ ትግል ነፃነነቱን ካወጀ አንድ ዓመት ማስቆጠሩን አስረድተዋል፡፡ ጉዞውም በሁሉም የአማራ ክልል በተመረጡ ታሪካዊ ቦታዎች የሚደረግ ሲሆን ተደራሽ በሚሆኑ ቦታዎች የምክክርና የትስስር መድረክ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የብልፅና ወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ መርከብ ተሰራ እንደገለፁት ትውውቅ ማድረግ፣ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችንና ዋጋ ለከፈሉ ወጣቶች ምስጋና ማቅረብ ሌላው የጉዞ ዓላማ እንደሆነ አክለው አስረድተዋል፡፡ በመጨረሻም ለወጣቶቹ የምሳ ግብዣ ከተደረገላቸው በኋላ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ጉብኝት አድርገዋል። ጉዞው ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚቀጥል ሲሆን የ “ዘንገና ሀይቅ” የአዊ ዞን ጉብኝት መጨረሻ እንደሚሆንም ተገልጿል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply