የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በጎንደር ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ሊያካሂድ መሆኑን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በጎንደር ከተማ ስብሰባ ጠርቷል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ህዝባዊ ውይይት እንደሚያደርግ በመግለጽ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ እንድትገኙ ሲል ጥሪ አድርጓል። የፊታችን ዓርብ የካቲት 17/2015 ዓ.ም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የስብሰባ አዳራሽ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ ህዝባዊ የውይይት መድረክ የተዘጋጀ በመሆኑን ኮሚቴው አስታውቋል።
Source: Link to the Post