You are currently viewing #የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የባህል ቡድን የመፍረስ አደጋ! ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የስምንቱ ማይቤት ጠገዴ የሰብዓ ወልቃይት ባህላዊና ታሪካዊ ክዋኔዎች ፣ ታላቅ አስታራ…

#የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የባህል ቡድን የመፍረስ አደጋ! ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የስምንቱ ማይቤት ጠገዴ የሰብዓ ወልቃይት ባህላዊና ታሪካዊ ክዋኔዎች ፣ ታላቅ አስታራ…

#የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የባህል ቡድን የመፍረስ አደጋ! ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የስምንቱ ማይቤት ጠገዴ የሰብዓ ወልቃይት ባህላዊና ታሪካዊ ክዋኔዎች ፣ ታላቅ አስታራቂ የሽምግልና ባህሎቻችን፣ የአክብሮት ፣ የአብሮነት ፣ የመተሳሰብ ፣ የአንድነትና የሐገር ወዳድነት ባህሎቻችን እስከዛሬ ድረስ እንዲረሱና መልካም ባህሎቻችን ትውልድ እንዳያውቃቸው እየተደረገ ቢቆይም አሁን ግን ባህሎቻችንን በነፃነት ለማስተዋወቅ ስምንቱ ማይቤት ጠገዴ ጎጅ እና መጤ ባህልን ትተን እኛ የአባቶቻችን ልጆች የአባቶቻችንን መልካም ባህል በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታወች እየተዘዋወርን ስናስተዋውቅ ቆይተናል። የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የባህል ቡድኑን ዝርዝር አላማና ባህላችን ሳይበረዝ ለትውልድ እንዴት ማስተላለፍ እንዳለበት በተለያዩ ጊዜያት በውጭ አገር ከሚኖሩ የዞኑ ተወላጆች ጋር ምክክር እና ቴሌቶን በማዘጋጀት ጭምር ለባህል ቡድኑ መቆየት ስራወች ሲሰሩ ቆይተዋል። በተለይም በአውሮፖ የሚገኙ አማራዎች በሙሉ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የባህል ቡድን ውብ ለዛ ያለው ባህላችን እኛን በማይመስል በመጤ ባህል እንዲቀየርና መሰረታዊ ባህላችን እንዲጠፋ ለዘመናት ፖለቲካዊ አድምታ ተሰጥቶት ሲሰራበት ቢቆይም ባህል ማንነት የሚወረሰው ከእናት ከአባት ፣ ከአያት ቅድመ አያት ነውና የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ህዝብ አማረኛ በመዝፈኑ ሲታሰር ፣ በአማራ በመፎከሩ ሲገረፍ ፣ በአማረኛ ሲያለቅስ እየተከለከለ እራሱን የሚገልፅበትን ባህሉን ተነፍጎ የቆየ መሆኑን በመረዳት ሰፊ ውይይት አድርገውበታል። ቢሆንም ግን ይህ የባህል ቡድን በሰሜን ጎንደር ባህልና ቱሪዝም እውቅና ከጠየቀ ከአራት አመት በሗላ እውቅና አግንቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ባህላችን በሰፊው ለማስተዋዎቅና ባህላዊ ሙዚቃዎችን፣ ዶክመንተሪዎችን፣ ድራማዎችን ፣ ቀልዶችን ፣ ፉከራና ሽለላዎችን በባህላዊ አልባሳት እና ቁሳቁስ እያጀበ አስተዋውቋል ። አሁንን ሁን ተብሎ ታግዶ የጥንቱ ወልቃይት ጠገዴ ተነፍጎበት መብቱ ጠለምትና ራያ ተከልክሎ መብቱ ባለ አባቱ ሀገር ልጅ ድሮ ከቤቱ እሱ ተመልካች ነው ዘፋኝ ጎረቤቱ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የባህል ቡድን ባህሉን በዚህ መልኩ እየተንቀሳቀሰ እያስተዋወቅን ሲያስተዋውቅ ቆይቷል። የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ባህል ቡድን አባል በዚህ መልኩ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ቢሆንም አሁን ላይ የመፍረስ አደጋ ገጥሞታል።ከአሁን በፊት የባህል ቡድኑን የሚመራው አቶ ተስፋሁን ማንዴ ነበር ። አሁን ግን እኒህ የባህል ቡድን አባላት ለሃገር ወገን አለኝታ የትግሉ አንድ አካል ሁነው በየጠረፉ በማንቃት እና አብሮ በመዝመት ደራሽ የላቸውም ተብሏል። በታወቂዎቹ የሃገራችን አቀንቃኞች በአርቲስት መሃሪ ደገፋው እና በአርቲስት የሻንበል በላይነህ ነጠላ ዜማዎች በባህላቸው አልባሳት በውዝዋዜ አድምቀው ሰርተዋል። በዚ አጀማመር የት ይደርሳሉ የተባሉ አባሎች በአንድ ግለሰብ በመመራታቸው ብቻ ከተለያዩ አካላት የተበረከተላቸውን ገንዘብ በመሰብሰብ እና የተሰጣቸውን የሙዚቃ መሳሪያዎች እንዲሁም በቡድኑ ስም ከተለያዩ ሃገራት ያሉ አድናቂ እና ደጋፊዎች የተላኩ ገንዘቦችንም በማጠራቀም የባህል ቡድኖቹን በትኖ የራሱን ሃብት በማካበት ራሱን ባለሐብት በማድረግ የባህል ቡድኑንን በትኖታል ሲሉ የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የባህል ቡድን አባላት ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል። ጉዳዩን ለማጣራት ለአቶ ተስፋሁን ማንዴ በእጅ ስልካቸው ብንደውልም ስልክ አያነሱም። ስለሆነም የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር እና የቱሪዝም ፅ/ቤቱ ጉዳዩን በማጣራት የባህል ቡድኑን ከመበተን ታደጉት ሲሉ የወልቃት ጠገዴ ጠለምት የባህል ቡድን አባላት ጥሪ አቅርበዋል። የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የባህል ቡድን ግንቦት 12/09/2015 ዓ.ም “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply