የወልድያ አማራ ወጣቶች ማህበር አብን የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚቀላቀል አስታወቀ፤ የረቡዕን ሰልፍ ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ…

የወልድያ አማራ ወጣቶች ማህበር አብን የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚቀላቀል አስታወቀ፤ የረቡዕን ሰልፍ ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ…

የወልድያ አማራ ወጣቶች ማህበር አብን የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚቀላቀል አስታወቀ፤ የረቡዕን ሰልፍ ተቀላቀሉ ሲሉም ጥሪ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አብን ጥቅምት 18 የጠራው ሰልፍ ማህበራችን ከተቋቋመበት የአማራ ህዝብን ሁለንተናዊ ጥቅም መከበር አላማ ጋር የማይጋጭና ተገቢ ሁኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም መበደል ከምንም በላይ የሚገዳችሁ የወልድያና አካባቢው ነዋሪዎች ከኛ ከወጣቶች ጋር በመሆን ንጉሳዊው ስርአት የአማራን ህዝብ ግፍ ግድ እንዲለውና ሌሎች አካላትም ጊዜ ገጠመን እድል ቀናን ብለው አማራው ህዝብ ላይ የሚያደርሱትን ግፍ እንዲያቆሙ የሚያሳስበውን ሰልፍ እንደሚቀላቀል አሳውቋል። ጊዜ ሰጠን ብለው በአማራ ላይ እልቂት እየፈፀሙ ያሉ ወገኖችም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የወጡበት ህዝብ ማለትም የኦሮሞ፣የትግራይ፣የቤንሻንጉልና የደቡብ ህዝቦች ከአማራ ጋር በመሆን እንዲታገሉ ሲል ማህበሩ አሳስቧል። በመሆኑም የፊታችን ረቡዕ መላው የወልድያና የአካባቢው ህዝብ በነቂስ በመውጣት በሰላማዊ መንገድ እና በትግስት የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲቆም የሚያሳስብ መልዕክት እንድታስተላልፉና የቀጣይ አቅጣጫ እንድቀይሱ የወልድያ አማራ ወጣቶች ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ለማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply