የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች በግንባር ለሚገኘዉ ጥምር ጦር የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረዉ ቀጥለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች በግንባር ለሚገኘዉ ጥምር ጦር የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረዉ ቀጥለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በወልድያ ከተማ አስተዳደር የየጁገነት ፣ የደፈርጌ ኪቢቃሎ ፣ የአዲስ ከተማ ፣የአደንጉር ገብርኤል ቀበሌ ነዋሪዎች በግንባር መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የወገን ጥምር ጦር በአላማጣ ከተማ በመገኘት ዛሬም የተለመደውን የስንቅ ድጋፍ በማድረግ ደጀንነታቸውን አሳይተዋል። በዛሬዉ እለትም የከተማዋ አመራሮች፣ ከተለያየ የህብረተሰብ ክፍል የተወጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች አላማጣ ከተማ በመገኘት ለወገን ሰራዊት ደጀንነታቸዉን አረጋግጠዋል ያለው የሰሜን ወሎ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply