የወሎ አማራ ማህበራዊ ወረቱን ተቀምቷል! ~~~~~~~ አሸናፊ ገናን ~~~~~~~~ በፀንፈኞች የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ምግብ፣ልብስ እና መጠለያን ይፈልጋሉ። ነገር ግን #የወሎ ፓለቲከኞች ደግሞ…

የወሎ አማራ ማህበራዊ ወረቱን ተቀምቷል! ~~~~~~~ አሸናፊ ገናን ~~~~~~~~ በፀንፈኞች የተፈናቀሉት ወገኖቻችን ምግብ፣ልብስ እና መጠለያን ይፈልጋሉ። ነገር ግን #የወሎ ፓለቲከኞች ደግሞ አዲስ ክልል የማዋለድ ስራን ለመስራት ደፋ ቀና እያሉ ናቸው። ይህን ሚዛናዊ ያልሆነ የፓለቲካ አስተሳሰብ ወደ ነበረበት ለመመለስ #ሰው መሆንን ይጠይቃል። በዕርግጥ የወሎ ፓለቲካ ልሂቃኖች ድብቅ ፍላጎት አለ።እርሱም ወሎየነትን ከአማራነት ማስቀደም ነው። ይሄ የተንሻፈፈ ስውር አስተሳሰብ ምንጩ #ሃይማኖታዊ አክራሪነት ነው። ጠንካራውን #የቤተዐማራ ህዝብ የማሳነስ ፓለቲካ ግን ተቀባይነት የለውም። የወሎ ፓለቲከኞች እጅግ ስር የሰደደ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ገብተዋል። በጥቂት ብአደናዊ ብሔርተኞች የተጀመረው #ወሎህብረት መዳረሻውን ክልላዊ ጥያቄ ላይ አድርጓል። ስለሆነም የወሎ ክልልነት አጀንዳ በጥቂት ብአዴኖችና የወሎ ህብረት አባላት ዕውን እንዲሆን እየተሰራ ነው። የወሎ ፓለቲካ መደራጃውን ዕምነት እስካደረገ ድረስ ራሱን ችሎ ክልል ሊሰየምለት አይገባም። ወሎ ክልል የመሆን አዝማሚያው እየተካሄደ ያለው በዕውነተኛ #የወሎ አማሮች አይደለም። በሰርጎ ገብ እና ተከፋይ ካድሬዎች የሚመሰረት አድስ መዋቅር ሊኖር አይገባም። የቤተ ዐማራ ህዝብ ነባር ዕሴቱን የሚያስቀጥልበት ፓለቲካዊ አስተሳሰብ እና አዲስ አከላል #ምስራቅአማራ የሚለው ክልላዊ ፕሮጀክት ዕውን ከሆነ ነው። ከዚህ የዘለለ ማህበራዊ ፋይዳ በሌለው የአክራሪዎች ክልል በመሰየም የቤተ ዐማራን ህዝብ ለቀውስ መዳረግ ተቀባይነት የለውም። ከሁሉም በፊት ግን ስለ ተፈናቃይ እና ተበዳይ ወገኖች ማህበራዊ ኪሳራ በጋራ እንቁም። እውነቱ ይሄው ነው። © አሸናፊ ገናን ሰ.ሜሪካ :- ሐምሌ 29/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply