የወረታ ወደብና ተርሚናል ባለፉት 10 ወራት 5 ሺህ 58 ቲኢዩ ኮንቴነር አስተናገደ

የወረታ ወደብና ተርሚናል ባለፉት 10 ወራት 5 ሺህ 58 ቲኢዩ ኮንቴነር አስተናገደ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል የገቢና ወጪ ዕቃዎች የተሟላ የሎጅስቲክስ አገልግሎት ለመስጠት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ፎገራ ወረዳ የሚገኘው የወረታ ወደብና ተርሚናል  የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ተባለ፡፡

27 ሔክታር መሬት በመረከብ በ2012 ዓ.ም የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታው ተጠናቆ ስራ መጀመሩ የሚታወስ ነው።

አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አንድ ዓመት ያልሞላው ይህ ወደብና ተርሚናል ባለፉት አስር ወራት ውስጥ 5 ሺህ 58 ቲኢዩ ኮንቴነር ማስተናገድ ችሏል፡፡

በ2013 በጀት ዓመት ስድስት ወራት 4 ሺህ 669 ቲኢዩ ኮንቴነር በማስተናገድ የላቀ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ የወደቡ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ እና የገቢ ጭነት ከታቀደው በላይ እየሆነ በመምጣቱ በወደቡ ላይ መጨናነቅ እንዳይፈጠር በቀጣይ አገልግሎት አሰጣጡን ተደራሽ ለማድረግ እና ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት  የማስተር ፕላንና የቢዝነስ ፕላን ጥናት ተከናውኖ ወደ ቀጣዩ የግንባታ ምዕራፍ ለመግባት እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ድርጅቱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በፎገራ ወረዳ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ እና አቅመ ደካማ ለሆኑ የአካባቢው ህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ኢባትሎአድ  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የወደብና ተርሚናሉ በአቅራቢያቸው መከፈቱ ከፍተኛ የጊዜ እና የገንዘብ ወጪ እንዳስቀረላቸው ደንበኞች የገለጹ ሲሆን የአካባቢው ህብረተሰብ በበኩላቸው በተለያየ የሙያ ዘርፍ በተፈጠረላቸው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post የወረታ ወደብና ተርሚናል ባለፉት 10 ወራት 5 ሺህ 58 ቲኢዩ ኮንቴነር አስተናገደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply