የወቅቱ አውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮን ከውድድሩ ውጪ ሆነች ! በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት…

የወቅቱ አውሮፓ ዋንጫ ሻምፒዮን ከውድድሩ ውጪ ሆነች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የስዊዘርላንድን የማሸነፊያ ግቦች ራሞ ፍሩለር እና ሩበን ቫርጋስ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ሻምፒዮን ጣልያን ብሔራዊ ቡድን ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

ስዊዘርላንድ በሩብ ፍፃሜው የእንግሊዝ እና ስሎቫኪያን አሸናፊ ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ የሚገጥሙ ይሆናል።

ያለፉት ሶስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር አሸናፊ ሀገራት ስፔን ፣ ፖርቹጋል እና ጣልያን በቀጣዩ ውድድር በጥሎ ማለፉ ተሸንፈው ተሰናብተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply