You are currently viewing “የወንድ፡ ልጅ፡ እናት፥ ታጠቂ፡ በገመድ፤ የልጅሽን፡ ሬሳ፥ አይቀብረውም፡ ዘመድ።” ሕዝባዊ የውይይት መድረኩ ቀጥሏል፤ የደቡብ ዕዝ ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቆ ምክንያቱንም አስረድቷል። እኛም ሕዝባ…

“የወንድ፡ ልጅ፡ እናት፥ ታጠቂ፡ በገመድ፤ የልጅሽን፡ ሬሳ፥ አይቀብረውም፡ ዘመድ።” ሕዝባዊ የውይይት መድረኩ ቀጥሏል፤ የደቡብ ዕዝ ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቆ ምክንያቱንም አስረድቷል። እኛም ሕዝባ…

“የወንድ፡ ልጅ፡ እናት፥ ታጠቂ፡ በገመድ፤ የልጅሽን፡ ሬሳ፥ አይቀብረውም፡ ዘመድ።” ሕዝባዊ የውይይት መድረኩ ቀጥሏል፤ የደቡብ ዕዝ ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቆ ምክንያቱንም አስረድቷል። እኛም ሕዝባችን የተሻለ መረጃ እንዲያገኝ ሰፋ አድርገን እንደሚከተለው ከትበነዋል፡፡ (ወልድያ ከተማ) በአሁኑ ወቅት ከ180 ሺህ በላይ ኗሪ ሕዝብ የሚገኝባት ወልድያ ከተማ ሁሉንም በአንድ ጊዜ በአንድ መድረክ ሰብስቦ ለማወያዬት ባትችልም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በምድብ በማወያዬት ሀሳብን በሀሳብ የማታገል ሂደቱ ሦስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል ዛሬ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም። በመድረኩ ከ700 በላይ የሰው ኃይል የታደመበት ሲሆን፥ ሀገራዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎን ቃኝቷል። በተለይም ሚያዝያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ መጥፎ አዝማሚያ ማምራት ጀምሮ የተገታውን የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን፣ ከፋኖ እና ከሕዝቡ ጋር ለማላተም ተከስቶ የነበረውንና የከሸፈውን ቀውስ ዋና ማጠንጠኛው አድርጓል። ለውይይቱ መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዶ/ር ዳዊት መለሰ ዘርፉን እያሰፋ ያለው ሕገ-ወጥነት ለህዋሓት የሎጅስቲክ አቅም በማቀበል፥ በሕገ-ወጥ ግንባታ፥ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጫናውን ምክንያት በማድረግ የዋጋ ንረትን በማባባስ ያለውን ችግር አውስተዋል። በጅምር የቆመውን የአስፋልት መንገድ ሥራ ለማስጀመር፣ ባዛር በማዘጋጀትም ለሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ኢንቨስትመንቶችን ወደ ከተማው ለማምጣት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴም ዶ/ር ዳዊት አመላክተዋል፡፡ የሰሜን ወሎ ዞን ም/ አስተዳዳሪ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጋሻው አሰሜ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ ሰሞኑን ፋኖን ትጥቅ ይፍታ፤ ይበተን ያለ አመራር የለም፡፡ የተባለው ሕግ ይከበር ነው ነው፡፡ ከየትም ያለ ጥፋተኛ ቡድን እየመጣ የመሸገባት ከተማ ናት፣ ይህን የታጠቀ ኃይል መስመር ለማስያዝ ሕዝቡ ከጎናችን ሊቆም ይገባል። የሚያስወራውም በተሠዉት ፋኖ ስም ገንዘብ የሚሰበስብ፣ በፋኖ ስም ለጠላት ጥይት የሚያቀብል እና የፖለቲካን ተልዕኮ አንግቦ ፋኖን ተቀላቀልኩ የሚል አካል ነው። እውነተኛ ፋኖዎቹ ግንባር ላይ ናቸው፤ ምሽግ ውስጥ ናቸው፤ ብለዋል፡፡ የመድረኩ ተሳታፊ ከስጋትና ካለፈ የሕይወት ተሞክሮ በማጣቀስ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን ሰንዝሯል፤ ወልድያ ውስጥ ጁንታው መቸ ጠራ? የእሱ አለመጥራት አይደለም ወይም የፀጥታ ኃይላችነን ለማጋጨት፤ አባትና ልጅ ሆነን በተግባር ያሳየን ሕዝብና የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን የተጣላ አድርጎ “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” የሚለውን ስልት ተጠቅሞ ነው የሚያጮኸው፤ “የወንድ፡ ልጅ፡ እናት፥ ታጠቂ፡ በገመድ፤ የልጅሽን፡ ሬሳ፥ አይቀብረውም፡ ዘመድ።” የተባለላቸው ዛሬ ብቻ ሳይሆን ጥንትም ከሀገር አቀፍ አልፎ ዓለም አቀፍ ተልዕኮ የሚወጣ ለሀገር ለሕዝብ ሕይወታቸውን የሚሰጡ የጸጥታ ኃይሎቻችንን ለሕዝብ ስስ ብልት በሆነ ጉዳይ የሚገቡና የሚያስመስሉትን ሁላችንም ተዉ እንበል፣ እንምከር ብለዋል ተሳታፊዎቹ። ከፋኖም ጋር ተያይዞ በእርግጥ በጨለማው ወቅትም ሲዘርፍ የነበረው ላለመጠየቅ ወደ ፋኖ የተጠጉ አንዳንዶች እንዳሉ እኛም እያስተዋልን ነው፡፡ እሱን እራሱ ፋኖ እንዲለይ ቢደረግ ሆኖም ግን ፋኖ በወቅቱ ወረራ ጊዜ ቡንኝ ጤፍ ከሆኑት አንዱ ነው፤ ቡንኝ ጤፍ ለችግር ጊዜ ቶሎ ይደርሳል፤ ይወደዳል፤ የመኸር ምርቱ ሲደርስ እሱ ይረሳል እና እንደዛ እንዳይሆን? ጦርነቱስ መቼ አበቃ? የትግራይ ወራሪ ቡድን እኮ ያለው ከእኛ ከአማራው ቀዬ ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል ታዳሚዎቹ። አመራሩም በትናንት አካሄድ አትሂዱ፤ እኛም በትናንት አካሄድ አንተቻችሁ፤ ነገን አስበን እንነጋገር። የማይለካችሁን ጥብቆ አታጥልቁ፡፡ ከተቀዳሚው ከንቲባው ውጭ ያላችሁት ህዋሓት ሲመራ በነበረበት ጊዜም ስለ ብሔርተኝነት እየሰበካችሁ መሪ ነበራችሁ፤ ዛሬ ደግሞ ስለ አንድነት ትሰብካላችሁ፤ እንዴት ተብሎ ነው ውስጣዊ አንድነትን የምታመጡት? ግጭት እንዳይፈጠር ለምን ቅድመ ትንበያ አትሠሩም? የሰው ልጅ በሽተኛ ሊሆን ይችላል፤ አሁን ግን ፖለቲከኛ ሰው ነው በሽታው፡፡ አርቆ በማሰብ እና በጥበብ ምሩን፤ የማኅበረሰብ አንቂ ነን በሚል ማኅበረሰብን ለማባላት የሚጥሩ፣ የጎሳ መሪ ነን በሚል ማኅበረሰብን የሚያለያዩ፣ ችግር ከመባባሱ በፊት መከላከያ ለምን አቅምና ስልት አይፈጥርም? ሕግን በማስከበር እና በፋኖ ስም ያለ ሌባ ካለ በመለየት ሂደት ለሕዝብ እና ለሀገር የሚዋደቀውን ፋኖ እና የሕዝቡን ሞራል የጠበቀ ምን ዓይነት ስልት ተቀይሷል? የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ጎልተው ወጥተዋል፡፡ በውይይት መድረኩ የተገኙት የደቡብ እዝ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ኮሌኔል ደጀኔ በተፈጠረው ክስተት በደቡብ እዝ ጠቅላይ መምሪያ ስም የወልድያ ከተማን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀዋል። እንኳን ዙ 23 እና ድሽቃ መተኮስ ጠጠር መጣልም ይከብዳል፤ ሆኖም መንገድ ለማስከፈት በተልእኮ ላይ የተሠዋብንን አባል ለማንሣት ተጨማሪ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ ወደ ሰማይ ለመተኮስ ተገደን ነው ብለው ምክንያት ያሉትን አስረድተዋል። ፋኖ የአማራ ሕዝብ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፋኖ ነው። እነ ጃጋማ ኬሎ ፋኖ ነበሩ። ትክለኛውን ፋኖ ማንም አይነቅፍም፤ ሆኖም ግን በተለያዬ የፀጥታ ኃይል የቡድን መሣሪያቸውን እንደያዙ የከዱትን፣ ወደ ግንባር ሳይሄዱ ተገቢ ያልሆነ መሣሪያ የያዙትን ስርዓት ማስያዝ አለብን። መዘጋጀቱ ችግር የለውም፤ ሁሉም መሰልጠኑ ክፋት የለውም፤ ክፋቱ ስርዓት አልበኝነትን አለመግታት ግን መጥፎ ነው፥ አይጠቅምም፤ እጁ ላይ ያለ ትጥቅ በአግባቡ እንዲመራ ማድረግ የሁላችን ድርሻ ይሁን። የሰነዱን ሙሉ ይዘት ከማየት ይልቅ ለፖለቲካ ንግድ የሚመቸውን ሐረግ በመምዘዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ስም ማጠልሸት ተገቢ አይደለም ብለዋል ኮሌኔል ደጀኔ፡፡ ዶ/ር ዳዊት መለሰ ከሁሉም ጋራ የተጠናከረ ውይይት በማድረግ ለሀገራችን ለከተማችን የሚጠቅመንን እንሠራልን፤ የፌስቡክ ዘመቻ ጭምርን በጋራ እንታገል፡፡ ፕሮፊሰር ክንደያ ሰውን ለመግዴል ወደ ጦር ግንባር መግባታቸውን እናውቃለን፤ እኔና መሰሎቼ ደግሞ ሕዝብን ብናገለግል ብለን ኃላፊነትን ተቀብለን መጥተናል፤ የፌስ ቡክ ዘመቻው ግን ተገቢውን ተግባር እንዳንሠራ ለማደናቀፍ እየጣረ ነው፡፡ እንግባባ፣ እንደማመጥ፣ በብስለት እንወያይይ፣ ካጠፋን አረሙን፣ ለጠላት በር የሚከፍቱ ወገኞቻችንን እንምከራቸው፡፡ ከፋኖ ወንድሞቻችን ጋር በጋራ መክረናል፤ በእነሱ የሚታየውን ክፍተት ቅድሚያ በራሳቸው እንዲፈቱ ተደርጓል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም የጋራ ጠላት በጋራ በመፋለም ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ሕገ ወጥነትን በጋራ በሰከነ የሕዝብንም ተሳትፎ ባማከለና ስሜቱን በማይጎዳ መልኩ በመግባባት፤ የመከላከያ ሠራዊታችንን ስምና ዝና የሚያጎድፉትን በጋራ ለመከላከል፤ ከመከላከያ ጋር እየተመካከረ በጋራ እየሠራ ያለውን የፋኖ ኃይል በማጠናከር፤ በፋኖ ስም የሚነግደውን በቅድሚያ ራሱ ፋኖ በአደረጃጀቱ እንዲያጠራና ችግሩ እንዲፈታ የጋራ ስምምነት ተደርሷል፡፡ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም የወልድያ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን

Source: Link to the Post

Leave a Reply