ምሁር ማለት እንደ ገብረመድህን አርዓያ፣ ነጋሲ በየነ፣ ጌታቸው ረዳ(ኢትዮጵያ ሠማይ) የረጅም ጊዜ ትግላችሁ ተሳክቷል፡፡
‹‹መቼም የትም አይደገም!›› “Never and Ever again”
የትግራዋይ ምሁራን በፅናትና በቆራጥነት ግፍነን በመታገል ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ቆማችሁ እውነቱን ለህዝብ በማሳወቃችሁ ትሪክ ሲያስታውሳችሁ ይኖራል፡፡ ገብረመድህን አርዓያ፣ ነጋሲ በየነ፣ ጌታቸው ረዳ(ኢትዮጵያ ሠማይ) የረጅም ጊዜ ትግላችሁ ተሳክቷል፣ በወደቁት ሠማዕታት ስም ምስጋና ይገባችኃል፡፡ ዛሬ የወያኔ አራጆችን አስወግደናል፣ነገ ደግሞ የኦነግ አራጆችን (ጆኖሳይድ) ድባቅ እንመታለን! ብዙ የህዝብ ልጆች በአንድ መቃብር ሥፍራ በህብረት በአንድነት ተቀብረዋል፤ ድብቁ የጅምላ መቃብር በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ይገኛሉ፣ ይፋ እንዲሆን በጋራ መታገል ታሪካዊ ኃላፊነታችን ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ ግድያ፣ እስራትና ሰደት ‹‹መቼም የትም አይደገም!›› “Nevere and Ever again”ብለን ቃል ኪዳን በመግባት ከስህተታችን ተምረንና ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ብቻ በመፍታት፤ ለቀጣዩ ትውልድ ሃገራችንን በፍቅርና በአንድነት ማስቀጠል ኃላፊነት አለብን እንላለን፡፡
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)የትግራይን ህዝብ ከ1975እኤአ እስከ 2020እኤአ ለአርባ ስድስት አመታት በግፍ ገዝተውታል፡፡ በዚያ ዘመን የመጀመሪያዎቹን የህወሓት መሪዎች የነበሩትን በግፍ ከገደሎቸው የትግራይ ልጆች ውስጥ ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ ተክሌ፣ አጽብሃ ዳኛው፣ ዶክተር አታክልት ቀጸላ ደም ደመ ከልብ ሆኖ አልቀረም፤ እውነተኛ ታሪካቸው ይዘከራል፡፡ ህወሓት ኢህአዴግ ለአለፉት ሃያ ሰባት አመታት የኢትዮጵያን ህዝብ በአንባገነንነት በግፍ አገዛዝ አስተዳድሮል፣ ብዙ ሽህ ሰዎች ገድሎል፣ አስሮል አሰድዶል፡፡
አንድ የትግራይ ተወላጅ ምሁር በአንድ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር መጠረት ወያኔ ይሄን ለምን እንደማይቀበለው እንገንዘብ፤“የህወሓት/ማሌሊት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው ሌላ አማራጭ መንገድ የማያውቁ በስታሊናዊ ጨካኝ አስተሳሰብ ተኰትኩተውና እንደ ዓሳራ ግመል ፊታቸውን ተሸብበው ያደጉ ናቸው:: መለስ ዜናዊም ብልጥ ነው:: ሆን ብሎ የህወሓት/ማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም በጭንቅላታቸው ውስጥ የገጠመላቸው ስለሆኑ ከዚያ አጥር ወጥተው ሌላ ሰፋ ያለ ዓለምና ሳይንስ የሚያዩበት መነፅር የላቸውም:: ቢተኩሱም! ቢነግሱም! ቢማሩም ያው ናቸው ምንም አይለወጡም:: ቀደም ብሎ በአእምሮኣቸው ከተገጠመላቸው የሶፍት ዌር ፕሮግራም ውጭ ሌላ የሚያውቁትና የሚናገሩት ሰላማዊ ቋንቋ የላቸውም:: ሁሉ ጊዜ “አካኪ ዘራፍ!! በለው ደምስሰው!! – ያዘው ልቀቀው” የሚሉትን ቃላቶች ብቻ ናቸው በአእምሮኣቸው የሚታዩባቸው:: ሕግ አይገዛቸው! ባህል አይገዛቸው! ታሪክ አይገዛቸው! ሀይማኖት አይገዛቸው! ጊዜ አይለውጣቸው! ዕድሜያቸው ልክ አንድ ዓይነት መዝሙር እየዘመሩ ጭንቅላታቸውን በማሌሊታዊ ሰይጣናዊ አስተሳሰብ እንደተቆለፈ ያልፋሉ:: በመሆኑም አሁን እየታየ ያለው ትልቁ አሳሳቢ ጉዳይ የህወሓት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው በማሌሊት ሶፍት ዌር ፕሮግራም መደንዘዛቸው ብቻ አይደለም ችግሩ:: ነገር ግን ከጫካ ይዘውት የመጡት መድሃኒት አልባ በሽታ ወደ ሌሎች ክልሎችም በፈጣን ሁኔታ እየተዛመተ መምጣቱ ነው:: ስለዚህ “ቤቱን ሳይቃጠል በቅጠል” እንደተባለው እኛም በተራችን ሳንታመም የመከላል ዘዴ መፍጠር ይኖርብናል፡፡”
የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ ሥልጣናቸውን በሰላማዊ መንግድ ያሸጋግራሉ ብሎ መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ እንደመተበቅ ይቆጠራል፡፡ ህወኃት በ46 ዓመታት የፈጸማቸው ወንጀሎች ተቆጥረውና ተዘርዝረው አይዘለቁም::
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ሕገ-መንግሥትና አስሩ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ህገ-መንግሥት በስብዕና ላይ ስለሚፈጸም ወንጀሎች፣ በይርጋ አይታገድም!!! በምህረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም!!! ስለዚህ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅነት ሰውን የመሰወር ወይም ኢሰብዓዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ለማቅረብ አስፈላጊውን መረጃዎች በማስቀመጥና በማከማቸት ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ እንደሚቻል ተረድቶ የሕገአራዊት ዘመንን ወደ ህገሰው ዘመን ማሻገር እንደ ሰው የሚያስቡ ዜጎች በዘርና ኃይማኖት ፍጅት ጠንሳሽ የመንጋና ጅምላ ቡድኖችን ለህግ የማቅረብ ኃላፊነት አለባቸው እንላለን፡፡
- በትግራይ ክልል ብዙ የትግራይ ተወላጆችን፣ የኢዲና የኢህአፓ/አህአሠ ሰራዊትን ገድለው ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡ ወያኔ የኢዲዩ አባላቶችን አስሮ ካሰቃያቸው በኃላ በነፍሰ ገዳይ ስኮዶቹ በነ ደብረጺዮንና ብስራት አማረ አማካኝነት ረሽነዋቸዋል፡፡
- የኢህአፓ አመራር አባሎችን እነ ፀጋዬ ገብረመድህን (ደብተራው)ና ሎሎችን ከመቀሌ እስር ቤት አስረው ካስቃቸው በኃላ ረሽነዋቸዋል፡፡ ለዚህ ግድያ ተጠያቂዎቹ የህወኃት አመራሮች ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣እስዬ አብርሃ፣ አባይ ፀኃዬ ወዘተርፈዎች በደም የተጨማለቁ ነፍሰ ገዳዬች መሆናቸውን አንርሳ፡፡ ህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት የፖለቲካ በትረ ሥልጣን ከያዙ በኃላ በሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ የጅምላ ግዳያዎች በመፈፀም እጃቸውን በደም የታጠቡ ብድኖች ናቸው፡-
- በኦሮሚያ በወለጋ፣ በበደኖ፣ በባሌ ከያዶት ወጣ ብሎ ብዙ ሰዎች ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡
- በሱማሌ ክልል ብዙ ሰዋች በኦብነግ ሥም ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡
- በአማራ ክልል ብዙ የወልቃት ተወላጆችን ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡
- በጋምቤላ ክልል ብዙ የአኝዋክ ተወላጆችን እነ አባይ ፀሃዬና ገብርአብ በርናባስ ገድለው በግሬደር ቆፍረው የቀበሩበት የጅምላ መቃብሮች ቦታዎች ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ድብቁ የወያኔና ኦነግ የዘርና ኃይማኖት ፍጅት (ጆኖሳይድ) ቀጥሎል ድብቁ የጅምላ መቃብር ተቆፍሮ እንዲወጣ ህዝብ ያላሰለሰ ትግል ማድረግ ይገባዋል፡፡ በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ግንባር (ህወሓት) እና በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦነግ)በግፍ የተፈፀመው በተለያዩ ክልሎች ትግራይ፣ አማራ፣ ፣ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ሱማሌ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በድብቅ የተፈፀሙ ግድያዎች እና ድብቅ የጅምላ መቃብሮች ተጋልጠው መውጣት አላባቸው እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ሕገ-መንግሥትና አስሩ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥቶች ህገ-መንግሥት በስብዕና ላይ ስለሚፈጸም ወንጀሎች፣ በይርጋ አይታገድም!!! በምህረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም!!!
- በ1984 ዓ/ም ከ300 በላይ የአማራ ዜጎች ላይ የዘርና የኃይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ በሐረር የጅምላ የዘር ጭፍጨፋ በበደኖ፣ ጋራሙለታ፣ ጨለንቆና እንቁፍቱ ገደል በኦነግ፣ ኦህዴድ፣ ህወሓት ግብረአበርነት በሰው ዘር ላይ የተፈጸመ ኢስብዓዊ ወንጀል ክስ በአማራ ክልል በኩል በአስቸኮይ ይቅረብ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ
https://www.Youtube.com/watch?v=E6UEc9WizBs/ ESAT human right eyewitness testimony the massacre of Bedeno 1992 Ethiopia
- የአማራ የዘር ፍጅት በ1990 ጉራፈርዳ በደቡብ ክልል ፕሬዜዳንት በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ትእዛዝ በጉራፈርዳ ብዙ ሰው ሞተ፣ ከመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቀሉ ወንጀለኞቹ እስካሁን ለፍርድ አልቀረቡም፡፡
https://www.Youtube.com/watch?v=EcZJIFUKx9M/Aug 25,2016
- የ1997ዓ/ም ህወሓት ኢህአዴግ ዘመን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በምርጫ ስበብ ሁለት መቶ ዜጎችን የተገደሉበትን ምርጫ አጣሪ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች ሆነው የተሸሙት ዳኛ ፍሬህይወትና ዳኛ ወልደሚካኤል ሪፖርታቸውን ለፓርላማ እንዳያቀርቡ በዶክተር አብይ አህመድ ዘመን መታገዳቸው ተነስቶ ለህዝብ ሪፖርቱ ይፋ እንዲሆንና የህግ ሉዓላዊነት በሃገሪቱ እንዲሰፍን ጅምሩን ሀ፣ሁ እንድንል ይሁን፡፡
- በ2003ዓ/ም በጋምቤላ የዘር ፍጅት አራት መቶ ሃያ አራት የአኝዋክ ዜጎች የዘር ፍጅት ተፈፀነባቸው፡፡ በጋምቤላ ክልል ዜጎች እስራት፣ ግርፋትና ሰደት በህወሓት ኢህአዴግ ባለስልጣናት ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በድርጊቱ አባይ ፀሓይዬ የፌዴራል ሚኒስትር፣ ዶክተር ገብረአብ በርናባስ ከህወሓት፣ ሜጀር ፀጋዬ በየነ ተካፍለዋል፡፡ ኡባንግ ሜቶ (Mr. Obang Metho is the founder and executive director of the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE).) የዘር ፍጅቱን በተጠቂዎቹ ወገን የክስ ቻርጅ በመቅረብ የዘር ፍጅቱን ፈፃሚዎች በአስቸኮይ ለህግ ማቅረብ የዘር ፍጅት እንደሚያስጠይቅ ገዳዬች መቼም ጊዜ ቢሆን ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ ያስተምራል እንላለን፡፡ On December 13, 2003, members of the Ethiopian military and other ethnic groups massacred more than 400 people in the town of Gambella. (http://www.anuakjustice.org/)
- በ2007ዓ/ም በሱማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦጋዴን ዜጎች ላይ የተፈጸመ የዘር ፍጅት በቆሬ፣ ጎዴ፣ዋርዳሂር፣ ፊቅና ፣ ደጋሃቡር ክስ በሙስጠፌ
- የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሲዳማ ህዝብ ላይ አዋሳ ሎቄ ህዝብ ፍጅት በህወሓት ኢህአዴግ እንዲሁም በኦዴፓ ብልፅግና 56 ሰዎች ግድያ አጣርቶ ወንጀለኞቹን ለህዝብ ማቅረብ ታሪካዊ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ሰኞ ሰኔ 22/ 2012 ዓም ‹‹የሃጫሉ ህልፈት ሚሊዮኖችን አስደንግጧል፤ በርካቶችን አስቆጥቷል። አሳዝኗል። ግድያውን ተከትሎም በተነሳ አለመረጋጋት ከ167 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቤት ንብረታቸው ዶግ አመድ ሆኗል።
- ሃምሌ 2012ዓ/ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአስራ አራት የአማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀመ የዘር ፍጅት
- ህዳር 2013ዓ/ም በሸዋ የደራ አማራዎች የዘር ተኮር ፍጅት ሠለባ በመሆን በተደጋጋሚ መጤ በመባል ይጠቃሉ፣ መፍትሄ አላገኙም፡፡
- በ2011 ዓ/ም የጁዋር መሃመድ የተከብቢለሁ የ86 (ሰማንያ ስድስት) ሰዎች ሞት፣ ንብረት ውድመትና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ወንጀሎች ተፈፅመዋል፡፡ ዶክተር አብይ የሞቾችን 82 ወንድና አራት ሴት፣በብሔር ሽንሸና ሃምሳ ኦሮሞ፣ ሃያ አማራ፣ ስምንት ጋሞ፣ ሁለት ስልጤ፣ አንድ ጉራጌ፣ ሁለት ሃድያ፣ አንድ አርጎነባና አንድ ብሄሩ ያልታወቀ፡፡ በሃይማኖት አርባ ክርስቲያን፣ ሠላሳ አራት ሙስሌም፣ አስራሁለት የሌላ እምነት ተከታይ ናቸው፡፡ ሰባስድስት በእርስበእርስ ግጭት የሞቱ፣ አስር በፀጥታ ኃይሎች እንደተገደሉ አስታውቀው ነበር፡፡
- በ2012 ዓ/ም ሃጫሉ ሁንዴሳ 187 ሰዎች ተገድለዋል የኦነግ ቄሮ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ቄሮ ድርጅታዊ የዘር ፍጅት ተዋናዬች በነፃና ገለልተኛ ኮሚሽን ተጣርቶ ለፍርድ ይቅረቡ!!! በዚህ የህቡዕ መፈንቅለ መንግሥት የፖለቲካ ሴራ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተደገሠው የዘር ፍጅት ሁለት መቶ ሠላሳ ዘጠኝ ሰዎች ሞት፣ ሁለት መቶ ሰዎች መቁሰል፣ ሁለት መቶ ሃምሳ መኪኖች መሰባበርና ሃያ መኪኖች መቃጠል፣ የአርባ አምስት ፎቆች መቃጠል፣ ብዙ ሽህ ቤቶች መቃጠል፣ መሠረቱ በዘርና በኃይሞኖት የማንነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የመንግሥት ሥራ ሲሆን በአመዛኙም የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ሠራዊቱና የፀጥታና የደህንነት መስሪያ ቤቱ ሠራተኞች እንዲሁም የክልል ሹማምንቶች የኦዴፓ/ብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ሃላፊነትና ተጠያቂነት መኖር አለበት እንላለን፡፡ ዓለም አቀፍ ትብብር በኢትዮጵያ መብት ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶችንና ዲያስፖራውን አስተባብረው አይሲሲ በገለልተኛ ተቆማት ፍርድ እንዲሰጥ ማድረግ የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው እንላለን፡፡
- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፡- ከዘር ፌዴራሊዝም ወደ ደም ፌዴራሊዝም !!! አጋንቱን አራጅ ከብልቃጡ ውስጥ ይዱሉት!!! ‹‹የአማራ ማስሚዲያ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ዜና መሠረት ጳጉሜ አንድ ቀን 2012ዓ/ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዘር ተኮር ፍጅት (ጆኖሳይድ) በመተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ኤባር ተብሎ የሚጠራ ቀበሌ አማራና አገው ሰማንያ ዘጠኝ ተወላጆች ላይ በስም ዝርዝር ተጠቁመው አሰቃቂ ዘር ተኮር ግድያ ተፈፅሞል፡፡ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ውስጥ የቤሻንጉል ህዝብ ንቅናቄ (ቤህን)፣ ጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉዴን) ከ ኦነግ ሸኔ ጋርና ከህወሓት ስውር እጅ ጋር በመጣመር የዘር ፍጅቱን አድርገዋል፡፡ የወረዳው ፖሊስ አስቀድሞ ቀበሌውን ለቆ ወጥቶ ነበር፡፡ በአለፈው ጊዜም ሃያ አምስት ሽህ የአማራና አገው ተወላጆች ተፈናቅለው እንደነበር የታወሳል፡፡ በ1983ዓ/ም ኦነግና ሻብያ የዛሬ ሠላሳ አመት በቤኒሻንጉል አሶሳ ሆስፒታልና ትምህርት ቤት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው እንደተቃጠሉ በታሪክ ይታወሳል፡፡››1
- በ2013 ዓ/ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በመገዝ ቀበሌ በታጣቂዎች 21 ሰዎች መገደላቸውን ታውቆል፡፡ ሞቾቹ ተፈናቅለው የነበሩ ወደ ቀበሌቸው ተመልሰው የሰፈሩ ሰዎች መሆናቸው አሳዛኝ ሆኖል፡፡
- በ2013 ዓ/ም በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ 61 የአማራ ተወላጆችን በመግደልና ቤታቸውን በማቃጠል የዘር ፍጅት ተፈፅሞል፡፡
- በጥቅምት 24 ቀን 2013ዓ/ም በኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ ዶክተር አብይ አህመድና የትግራይ ክልል የጦር አበጋዞች መንግስት ዶክተር ደብረፂዮን ገብረማርያም ኢትዮጵያን ለሃያ ሰባት አመታት በግፍ ከገዛ በኃላ ከሥልጣኑ ወርዶል በዚህም ብሶቱ በትግራይ ውስጥ የሚገኘውን የሃገሪቱን የፌዴራል መንግሥት የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ላይ የመሣሪያ ጥቃት በመፈፀም፣ የሃገሪቱን የጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በመማረክ የተራ ወንበዴ ሥራ ሰርቶል፡፡ በህወሓት ሠራዊት በማይካድራ በአማራ ተወላጆች ላይ በገጀራ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሞል፣ ብዛታቸው ከ350 እስከ 500 ሰዎች ይገመታል፡፡ የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት አባሎችን በተለይም የአማራ ተወላጆችን በመግደልና መሳሪያውን በመዝረፍ ዳግም ወደ ሥልጣን መንበራችን እንመለሳለን በሚል የንፁሃን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል፡፡
- በህዳር 2013 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል በሸዋ በደራ የአማራ ተወላጆች ላይ የዘር ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ብዙ ሰዎች ሸሽተው አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
አንድ ሚሊዮን የኦሮሞ ህዝብ ከሱማሌ ክልል ተፈናቅለዋል!!! ግማሽ ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ከተለያዮ ክልሎች ተፈናቅለዋል!!! በደቡብ ክልል 450 ሽህ ጌዲዬ ህዝብ ተፈናቅለዋል!!! የወያኔ መንግሥት የከፋፍለህ ግዛ ዘመን አብቅቶል!!! የወያኔ የኮንትሮባንድ ንግድ ሲባል ህዝብ አይፈናቀልም!!! ኤርትራን ያስገነጠለ፣ የባህር በር ሃገሪቱን ያሳጣ፣ ባድሜን አሳልፎ የሸጠ የወያኔ ሥርዓት በኢትዮጵያዊ ትግራይ ወጣቶች ትግል ይገረሰሳል!!! በቃ ፍየል ሲሰባ፣ ሾተል ይልሳል!!! ሰው ታሞ እንጅ፣ ፈርቶ አይሞትም! የተፃፈልንን እኖራለን!!! ህዝባዊ ዲሞክራሲዊ ጋርድ ሆነን ለሃገራችን ዘብ እንቁም፡፡ ወያኔ ታግለን የያዝነውን የፖለቲካ ሥልጣን አናስነጥቅም፣ በማለት የትግራይን ህዝብ በስብኣዊ ጋሻነት ይዞል፡፡ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ወንድሞቹና እህቶቹ ጎን ቆሞ ወያኔን የሚፋለምበት ጊዜ አሁን ነው እንላለን፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በሚኖሩ ዜጎች በተለይም በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ትኩረት ተሠጥቶት ወንጀለኞቹ ለፍርድ ቀርበው አስቸኮይ እርምጃ ለወሰድባቸው ይገባል እንላለን፡፡ የኦሮሞ ድርጅቶች ኦነግ፣ ኦነግ ሸኔ፣ ኦፌኮ ወዘተ በኦሮመያ ክልል ውስጥ አንዱን ነዋሪ አንዱን ሠፋሪና መጤ
ሠላም ለኢትዮጵያ!!
ፍርድ ለህወኃት ደም መጣጮች፡፡
ፍየል ሲሰባ፣ ሾተል ይልሳል!!!
ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው? For Whom The Bell Tolls?
የትናንቱ ውጊያ ከኮረብታው ላይ፣ ሲያውድ የባሩድ ሽታ፣
በዛ ቅዝቃዜ! ሆድ ሲንቦጫቦጭ፣ ሙቀት በብርድ ሲረታ፣
የጠመንጃ ጩኸት፣ የተኩስ እሩምታ ሰማየ ሰማያቱን ሲነድለው
በዛ ውጊያ የጦር ጀነራሎቹ ትክክል ነበሩ …ማን አለና?
ለባድማ መሬት ብሎ ሰው ይሞታል፣ ግን ለምን? እነሱም አያውቁማ!!!
ያመረቀዘ ቁስላችን፣ ለእነሱ ክብርና ኩራት ሆናቸው!!!
በባድማ! ያ ሁሉ የደሃ ልጅ ረግፎ፣ የአምስቱ የጦር መኮንኖቹ ሲሳይ፣
በሹመት ላይ ሹመት፣ በሜዳልያ ላይ ሜዳልያ፣ በበላይ ላይ በላይ፣
የእብደትና ህመም ደዌችንን፣ በእርግጥ ያውቃሉ ያሳለፉነውን ስቃይ፣
ታዲያ! ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?
ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ካጠፋ፣
የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ
ታዲያ ደውሉ የሚያቃጭለው ለማን ነው? ኩኩሉ ሳይል አውራ ዶሮው፣
የደሃ ልጅ የሆናችሁ፣የእናንተን ዕጣ ፈንታ ልንገራችሁ፣
ከመሞታችሁ በፊት፣ ቀኑን ተሠናበቱ፣ ሰማየ ሰማያቱን እያያችሁ፣
በመጨረሻ እስትንፋሳችሁ፣ ትሁን ንዛዜችሁ ለእናታችሁ!!!
ነፍሳችሁ ስታርግ፣ ትሰወራለች ቀስ ብላ ጥላችሁ፣
በድቅድቁ ጨለማ፣ በነጎድጎዳማ መብረቅ ሲርድ ሰማይ፣
ለተቀጨ ዓላማችሁ ብካይ፣ አጎሩ ለረገፈ መንፈሳችሁ ታላቅ ራዕይ፣
ነፍስ ረቂቅ ሚስጢር፣ እንግዳ ነገር ሆነች ዐይናችሁ ላይ፣
ፀጥታው ባርቆ ይሰማል፣ በዝምታ አድምጥ የልብህ ትርታ ካንተ ስትለይ፣
የብርሃን ጨረር ፈንጥቃ ለስንብት፣ በዚህ ዓለም ከተስፋ ሌላ አረ ምን ሊታይ?
ሞታችሁን ባናይ እንኮን፣ ያዩት ይመሰክሩ የሌት ጨረቃ የቀን ፀሃይ
የዓይነ ስውር ዓይን ሲበራ፣ ሞት በህይወት ልትረታ ትንሳኤ ላይ፣
ታዲያ እማማ፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?
ጊዜው እንደ ወንዝ እየገዘፈ፣ እንደ አውሎ ንፋስ እየከነፈ፣ ነፍስ ነፍስን ከገፋ፣
የባህር ማዶ ቄጤማ፣ ሲወድቅ ሲነሳ በተስፋ
ድህነትና ርሃብ፣ በሽታና ሰደት ሳናጠፋ
በቌንቌ ተካለን፣ ማኛ ጤፍ ዘር ስንነፋ
ጦርነት አርግዘን ስናናፋ፣ ድንቁርናችን ምነው ከፋ
ዛሬም ወገን በወገን ላይ፣ በዘር ጦር ሰብቀን ስንነሳ፣
የባደማ ፆረና ሞት አልፈን፣ በወልቃይት፣ራያና አፋር ጦር ሜዳ ደንገላሳ፣
ታዲያ እማዬ ደውሉ የሚደወለው ለእኛ ሞቾች ነው? ትንቢተ ትንሣዔ ራቀ ምነው?
ጦርነት ‹መቼም የትም አይደገም!!!› ሳንል! መፈናቀላችን ስለምን ነው! ሰደቱንስ መች ለመነው?
የሰው ልጅን ከኃጢያቱ እንፈውሰው፣ ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?
ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው? ደውሉ የሚደወለው ለማን ነው?
(ኦክቶበር 10 ቀን 2018 ተፃፈ)