የዉህድ ኢትዮጵያዊ እና የዲቃላ ኢትዮጵያዉያን ነገር ፥- ደም ወይስ አስተሳሰብ? ====== ሸንቁጥ አየለ ====== 1/ ዉህድ ኢትዮጵያዊ ===≈=========== -> ከሁለት ወይም ከሁለ…

የዉህድ ኢትዮጵያዊ እና የዲቃላ ኢትዮጵያዉያን ነገር ፥- ደም ወይስ አስተሳሰብ? ====== ሸንቁጥ አየለ ====== 1/ ዉህድ ኢትዮጵያዊ ===≈=========== -> ከሁለት ወይም ከሁለት በላይ ከሆኑ ነገዶች ይወለዳል።ይሄ ኢትዮጵያዊ የተከበረ፡ እራሱን የሚያከብር፡ ሁሉንም የተገኘባቸዉን ነገዶች የሚወድ ፡ ከነገዳዊ ማንነቱ በላይ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን የሚያስቀድም ነዉ። -> ይሄ የተከበረ ኢትዮጵያዊ ይባላል። ጊዜ አይቶ እንደኛዉን ማንነቱን ክዶ ወደ አንዱ ማንነቱ አያደላም። ወገኖቹ እንዲስማሙ ሁሉንም ያስተምራል፡ አልሰማ ያለዉን ይወቅሳል፡ እግዚአብሄር ብሎ ስልጣን ላይ የተቀመጠ እንደሆነ ለማንም አያደላም፡ ለእናቱ ወይም ለአባቱ ነገድ አያደላም ፡ ለሰዉ ልጆች ሁሉ እኩል ይፈርዳል። 2፡ ዲቃላ ፥- ከልዩ ልዩ ነገድ በመምጣት ከዉህድ ኢትዮጵያዊ አንድ ነዉ። ሆኖም ከተከበረዉ ዉህድ ኢትዮጵያዊ በተቃራኒ ዲቃላ ባህሪ ያለዉ ሰዉ አንዱን ወገኑን ክዶ አንዱን የሚያነግስ ነዉ።የእናቱን ወይም የአባቱን ወገን ክዶ አንዱን ማንነቱን ይዞ ህዝብ የሚያጫርስ፡ ጸብ በህዝቦች መሃል የሚዘራ ፡ ዘመን ለሆነለት ነገድ ጭራዉን የሚቆላ ነዉ። ከሃዲ፡ የበታችነት የሚሰማዉ፡ በነገዶች እኩልነት የማያምን ስለሆነ አንዱን ማንነቱን ክዶ አንዱን ማንነቱን ብቻ አንጠልጥሎ የሚሮጥ ዲቃላ ነዉ።ከትልቁ ኢትዮጵያዊ ማንነቱ ይልቅ የአንድ ወገን ነገዱን ቆጥሮ ወደ እንድ ወገን በመሸጎጥ ሌላዉን ነገዳዊ ማንነቱን ለማጥፋት የሚራወጥ ነዉ። ለነዚህ አይነት ሰዎች ማሳያ የሚሆኑ በርካታ የኦነግ/ኦህዴድ እና የህዉሃት አመራሮች አሉ። ግማሹን ማንነታቸዉን ክደዉ ወደ እንድ ማንነታቸዉ ዉስጥ ተሸጉጠዉ በተወለዱባቸዉ ነገዶች መሃል ልዩነት እየዘሩ ህዝብ የሚያጫርሱ ብሎም ኢትዮጵያዊ ማንነታቸዉን በጭቃ የሚረግጡ ዲቃሎች ሞልተዋል። መለስ ዜናዊ ኢርትራዊ ማንነቱን ክዶ ኢርትራን ከኢትዮጵያ ያስገነጠለ፡ አቢይ አህመድ አንዱን ማንነቱን ክዱ የአማራን ህዝብ በመጨፍጨፍ ላይ የተጠመድ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ምድር ሰዎች እንዳይኖሩ እየሰራ ያለ ነዉ። ==≈====== በተከበሩት ዉህድ ኢትዮጵያዉያን እና ዲቃሎች መሃከል ያለዉ ቁልፍ ልዩነት ዲቃላዎች እራሳቸዉን የሚጠሉና በበታችነት ስሜት የሚሰቃዩ ስለሆነ አንዱን ማንነታቸዉን ቆርጠዉ በመጣል ፈዉስ የሚያገኙ ይመስላቸዋል።በዚህ የበታችነት ስነልቦናዊ ደዌም የተነሳ ኢትዮጵያዊነትን ሳይሆን መርዛማ የጎሳ ፖለቲካን ያራግባሉ። የተከበሩት ዉህድ ኢትዮጵያዉያን ግን ማንነታቸዉን የሚያከብሩ፡ የወጡበትን ነገድ ሁሉ የሚወዱ ብሎም ከፍ ያለ ማንነት ስላላቸዉ ከፍ ያለዉን ኢትዮጵያዊነት በታላቅ አክብሮት የሚያራምዱ ናቸዉ። ======= መደምደሚያ ========= ሲጠቀለልም አንድን ሰዉ ዉህድ ኢትጵያዊ ወይም ዲቃላ የሚያስብለዉ ከተለያዩ ነገዶች መወለዱ አይደለም። አስተሳሰቡ እንጂ። በደም መወለድስ ሰዉ ሁሉ የተለያዬ ነገዳዊ ደም የለዉም።የአንድ የአዳም ደም ያለዉ ፍጥረት ነዉና። ስለሆነም በደም መወለድ ተቆጥሮ አንድ ሰዉ ዲቃላ ነዉ ወይም ዉህድ ነዉ አይባልም። ምክንያቱም ከአንድ ነገድ ተወልደዉም የዲቃላ ሀሳብ እና አስተሳሰብ ያላቸዉ እራሳቸዉን፡ ነገዳቸዉን እና ኢትዮጵያዊ ማንነታቸዉን የሚጠሉ ብዙዎች አሉና። ለእነዚህ መልካም ምሳሌ የሚሆኑት ብአዴናዉያን እና አብናዉያን ዲቃሎች ናቸዉ። በመሆኑም የዉህድ ኢትዮጵያዊ እና የዲቃላ ኢትዮጵያዉያን ነገር የደም ጉዳይ ወይም ከልዩ ልዩ ነገድ የመወለድ ጉዳይ አይደለም። የአስተሳሰብ ጉዳይ እንጂ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply