የዋስትና ገንዘብ ተከፍሎላቸው ከዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መፍቻ የተጻፈላቸው የአደራ እስረኛ ናችሁ የተባሉት እነ ጥላሁን አበጀ ከህግ ውጭ በፖሊስ እምቢተኝነት ዛሬም አልተፈቱም። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

የዋስትና ገንዘብ ተከፍሎላቸው ከዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መፍቻ የተጻፈላቸው የአደራ እስረኛ ናችሁ የተባሉት እነ ጥላሁን አበጀ ከህግ ውጭ በፖሊስ እምቢተኝነት ዛሬም አልተፈቱም። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በመተማ ወረዳ ፍ/ቤት ከተፈቱ የሰነበቱት እነ አርበኛ ጥላሁን አበጀ፤ ከባ/ዳር ወደ መተማ ተወስደው የአደራ እስረኛ ናችሁ የተባሉት 5ቱ ወጣቶች ታህሳስ 21/2015 በምዕራብ ጎንደር ዞን ፍ/ቤት ቀርበው ዐቃቢ ህግ አልቃወምም በማለቱ በዋስትና እንዲፈቱ መወሰኑ ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ለእያንዳንዱ አምስት አምስት ሽህ ብር ዋስትና ታህሳስ 21/2015 መክፈላቸው ታውቋል። ይሁን እንጅ እነ አርበኛ ጥላሁን አበጀ፣ ናትናኤል ዘነበ፣ ሀ/ማርያም ክብረት፣ ጌትነት እሸቱ እና መታገስ ጸጋው ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ታህሳስ 22/2015 ከሰዓት ድረስ ከህግ እና ከፍ/ቤት ትዕዛዝ ውጭ የዞን ፖሊስ ምክክር ያስፈልጋል በማለቱ አልተፈቱም ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply