የዋጋ ንረት እና የኑሮ ውድነት በሶማሌ ክልል

https://gdb.voanews.com/1448D5F9-E810-4D19-B990-B9878066A50B_w800_h450.jpg

የሶማሌ ክልል መንግሥት በክልሉ የምግብ ነክ ዋጋ ንረትን ለመከላከል ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ። ክልሉ ምግብ ነክ ሸቀጦችን የሚያስመጣና የሚያከፋፍል መንግሥታዊ ተቋም ለማቋቋምም ወስኗል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ግን ሃሳቡን አይደግፉም። በክልሉ በአንድ ሳምንት ውስጥ የታየው ድንገተኛ የዋጋ ጭማሪ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኗል።

የሶማሌ ክልል ባለፈው አንድ ሳምንት በክልሉ የምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ መታየቱን ተከትሎ የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ይጠቅማል ያላቸውን ውሳኔዎች ማሳለፉን አስታወቀ። የክልሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ በሽር ሻፊ ክልሉ 4 አንኳር ውሳኔዎችን እንዳሳለፈ ነው ያስታወቁት።

የክልሉ ምግብ ነክ ሸቀጦች በዋናነት ድንበር ተሻግሮ ካሉ ጎረቤት ሃገሮች የሚገዙ መሆናቸው የገለጹት አቶ በሺር ይህም በባንኮች በበቂ ሁኔታ እየቀረበ አይደለም ያሉትን የውጭ ምንዛሪ ክፍተት ለመድፈን በጥቁር ገበያ የዶላር አቅርቦት ላይ ጥገኛ እንደሆነና ለዚህም ባንኮችንና ሌሎች የገንዘብ ዝውውርና ምንዛሪ ተዋናዮች ላይ ቁጥጥር ማድረግን እንደ አንድ እርምጃ መወሰዱን ነው የሚናገሩት።

በዚህም በጥቁር ገበያው በአንድ ሳምንት ከ10 ብር በላይ ጭማሪ ያሳየው የዶላር ምንዛሪ ወደቀድሞው መመለስ መጀመሩን አቶ በሽር ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply