የዋጋ ጭማሬ የታየበት የበዓል ግብይት

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 የዘንድሮው የበዓል ግብይት በሁሉም መልኩ የዋጋ ጭማሬ የታየበት መሆኑን ሸማቾች ተናገሩ። የፋሲካ በዓልን በማስመልከት በተለያዩ አካባቢዎች በተዘጋጁ ኤግዚቢሽኖች፣ የበሬ፣ የበግና ፍየል፣ የዶሮ ግብይት ስፍራዎች የዋጋ ንረት ታይቷል፡፡ ለአብነትም የበሬ ዋጋ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ10 እስከ 15 ሺህ ብር ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተገለፀው፡፡ 

ለበሬ ዋጋ መጨመር በማጓጓዝ ሂደት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪና የእንስሳት መኖ ዋጋ መናር ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸው ሻጮች ተናግረዋል። በበግና ፍየል ንግድ ላይ ተሰማርተው ላለፉት 20 ዓመታት የሰሩት አቶ አሸናፊ ወልደሰንበት ግን በዘንድሮው ገበያ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እንደሌለ ይናገራሉ።   በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ የአዋቂና ህጻናት የባህል አልባሳትን ለሽያጭ ይዘው የቀረቡት ወይዘሮ አለሚቱ ደንደና ጥሩ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘን ቀርበናል ብለዋል።

ይሁን እንጂ በግብይት ላይ የነበሩ ነዋሪዎች የበአል ገበያው በአብዛኛው ጭማሬ ታይቶበታል ሲሉ ተናግረዋል:: ሸማቾች እንደሚሉት የዘንድሮው የበዓል ግብይት በሁሉም መልኩ የዋጋ ጭማሬ ታይቶበት የበርካቶችን የመግዛት አቅም ፈትኗል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply