የዌልሷ ልዕልት ካትሪን በካንሰር መያዟን ይፋ አደረገች፡፡የእንግሊዝ ንጉሳዊ ቤተሰብ አልጋወራሽ የልዑል ዊሊያም ባለቤት የሆነችዉ የዌልሷ ልዕልት ካትሪን በካንሰር መያዟን ይፋ አድርጋለች፡፡በቪ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/ivy6WkF_OdbKS9LTPOTgShCDmQDRKvzHo0Q-cMbTeycRX76dUibIa_S7MqB_QGI1vLoJjolw4N3CaejpcmcbZJ3QYxgfk8McWbcnqpEor2SWgg4KkZILU2eXZzeg1GA3MMtCsQ-bdrWcwFNiqcJ4SPsDxpoGTk7bunhBUILOER4pW8kRjBIBpK1Ivz0TSR0qKCqifqBK4Mvv7zcKVw-pPX3mAnRFvb5IgkrWg3mzwq5OQ5h_9KOjD3aSaC5D3Osd3kbOPeLTZvbmHh6-fwu2mT7oJJXdAXMCHyCVuS04GnIFYzACyMxSDtoPNa1V8ESgP7IH8P0oo5EGW2ZoSdyjgA.jpg

የዌልሷ ልዕልት ካትሪን በካንሰር መያዟን ይፋ አደረገች፡፡

የእንግሊዝ ንጉሳዊ ቤተሰብ አልጋወራሽ የልዑል ዊሊያም ባለቤት የሆነችዉ የዌልሷ ልዕልት ካትሪን በካንሰር መያዟን ይፋ አድርጋለች፡፡

በቪድዮ ባስተላለፈችዉ መልዕክትም ካንሰሩ በመጀመሪያዉ የዕድገት ደረጃ ላይ መሆኑን ገልጻ የካንሰሩን ምንነት ከመግለጽ ግን ተቆጥባለች፡፡

ከባድ ሁለት ወራትን ነዉ ያሳለፍነዉ ፤ዜናዉም እጅግ አስደንጋጭ ነዉ ስትል ገልጻለች፡፡

ነገር ግን ‹‹ደህና ነኝ ዕለት ከዕለትም እየጠነከርኩኝ ነዉ›› ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች፡፡

ስለ ካንሰሩ ዝርዝር መረጃ ባይኖርም ግን የኬንሲንግተን ቤተመንግስት ልዕልቷ ሙሉ ለሙሉ ወደ ጤናዋ እንደምትመለስ እርግጠኛ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

ልዕልቷ እንደገለጸችዉ ከሆነ ፤በጥር ወር ላይ ቀዶ ህክምና አድርጋ የነበር ቢሆንም በሰዓቱ ካንሰሩ መኖሩ እንዳልታወቀ ነዉ የተናገረችዉ፡፡

‹‹ከቀዶ ህክምናዉ በኋላ ግን የመጡ ዉጤቶች ካንሰር መኖሩን በማሳየታቸዉ ፤ ሀኪሞቼ የቅድመ መከላከል ኬሞቴራፒ ብወስድ የተሻለ መሆኑን ስለነገሩኝ አሁን የመጀመሪያዉን ዙር ህክምና ጀምሬያለሁ›› ብላለች፡፡

የ 42 ዓመቷ ልዕልት በካንሰር ተይዘዉ ያሉ ሌሎች ሰዎችን አስባለሁ ያለች ሲሆን፤ ‹‹በየትኛዉም ደረጃ ቢሆን በዚህ ህመም ዉስጥ ያላችሁ ሁላችሁም መቼም ተስፋ እንዳትቆርጡ፡፡ብቻችሁንም አይደላችሁም፡፡››ስትል በቪድዮ መልዕክቷን አስተላልፋለች፡፡

በእስከዳር ግርማ

መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply