የውሀ ጉድጓድ ለማጽዳት የገባው ወጣት ህይወቱ አለፈ።በሸገር ከተማ ለገዳዲ ጥልቀቱ 15 ሜትር ገደማ የሆነ የዉሀ ጉድጓድ ዉስጥ ጉድጓዱን ለማጽዳት የገባው የ30 ዓመት ወጣት ህይወቱ አልፏአል…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/SxNDLuadvTN_mb423r0lnZx1FGwpKwBmcom8Q46s_wVcs9VU54-A4fV6hQK9ymgZJuSRJHntQfNz_OZYXfBRZG5SjpoTVLozUwW7H8aeTu643K0ZVzeTEvhtRMimxtqRMLeHRAw8G6FajHsGhddQY80Uk0p8Ng_P_20NEkRuvKLDXcEeb_zzU0lNys4ute5c4fMQcVEApJzODCG3ut2JmxrQuhwlaOiVdxLbHrDTNoCxP31FiJVsamy6Q691gFLp3Y3Qp0TfxCb6INbd2PAneOdIYfOKCg4nvg2zkPpgpDsE5Uc9ez8zpw5YyQzG_UJIiNCSOP8f_ImilLU-CZf1XQ.jpg

የውሀ ጉድጓድ ለማጽዳት የገባው ወጣት ህይወቱ አለፈ።

በሸገር ከተማ ለገዳዲ ጥልቀቱ 15 ሜትር ገደማ የሆነ የዉሀ ጉድጓድ ዉስጥ ጉድጓዱን ለማጽዳት የገባው የ30 ዓመት ወጣት ህይወቱ አልፏአል ተባለ።

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር የኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አስከሬኑን ከጉድጓድ ዉስጥ አዉጥተው ማስረከባቸው ተገልጿል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኘነት ሃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት እንዲህ ባሉ ጥልቅ ጉድጓዶች ዉስጥ ጉድጓዱን ለማጽዳትና ለመሰል ስራዎች አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በፊት የደህንነት መስፈርት ባለመጠበቃቸዉ ምክንያት ያጋጠሙ አደጋዎች መኖራቸው ጠቁመው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply