
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ ልማት ፈንድ ጽህፈት ቤት ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የአምስት ሚሊየን ብር ቦንድ ገዛ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ምክትል ዋና ዳሬክተር አቶ ታገል ቀኑብህ ÷ግድቡ ለአገርና ለወገን የሚተርፍና ለትውልድ አሻራ የሚያስቀምጥ ትልቅ ስራ ነው ብለዋል።
ለሕዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት የዚህ ትልቅ ታሪክ ባለቤት ናቸው በማለት ገልጸው÷ እያደረጉት ላለው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
የውሃ ልማት ፈንድ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ዋና ዋኬ ÷ተቋሙ ለግድቡ ግንባታ የቦንድ ግዢ ሲፈጽም ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑንና በቀጣይም ለግድቡ ግንባታ የሚያደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
The post የውሃ ልማት ፈንድ ጽህፈት ቤት ለሕዳሴ ግድብ የአምስት ሚሊየን ብር የቦንድ ግዢ ፈጸመ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.
Source: Link to the Post