የውስጥ የፀጥታ ችግሮቻችንን በፍጥነት በመፍታት ግብፅ በቀጣይ ለምትሰነዝራቸው እያንዳንዱ አሉታዊ ጉዳዮች ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ያስፈልጋል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳሰቡ፡፡

የእናት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ ጌትነት ወርቁ ለአሐዱ እንዳሉት ግብፅ በየጊዜው ለምታወጣው መረጃ ኢትዮጵያ ማፈግፈግ የለባትም፤ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉን አቀፍ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም በሀገሪቷ ውስጥ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን በፍጥነት በመፍታት ግብፅ በቀጣይ ለምትሰነዝራቸው ሴራዎች ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ዋናው ፀሐፊው ገልፀዋል፡፡

በሀገር ውስጥ የሚስተዋሉትን የፀጥታ ችግሮች መፍታት ከተቻለ ግብፅ በየጊዜው ለምታነሳቸው ፕሮፓጋንዳዎች ኢትዮጵያ ለመቋቋም እንደማይከብዳት የሚያነሱት ደግሞ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ኅብረት ሊቀ-መንበር አቶ ገብሩ በርሄ ናቸው፡፡

ቀን 06/08/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

The post የውስጥ የፀጥታ ችግሮቻችንን በፍጥነት በመፍታት ግብፅ በቀጣይ ለምትሰነዝራቸው እያንዳንዱ አሉታዊ ጉዳዮች ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ያስፈልጋል ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሳሰቡ፡፡ appeared first on አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን.

Source: Link to the Post

Leave a Reply