የውጭ ሚዲያ የኢትዮጵያ ወኪሎች እየታሰሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ወደ መረጃ እገታ እያመራች ነው፡፡           አሻራ ሚዲያ    ታህሳስ19፣ 2013ዓ.ም ባህርዳር ሮይተር…

የውጭ ሚዲያ የኢትዮጵያ ወኪሎች እየታሰሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ወደ መረጃ እገታ እያመራች ነው፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ19፣ 2013ዓ.ም ባህርዳር ሮይተር…

የውጭ ሚዲያ የኢትዮጵያ ወኪሎች እየታሰሩ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ወደ መረጃ እገታ እያመራች ነው፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ19፣ 2013ዓ.ም ባህርዳር ሮይተርስ የካሜራ ባለሙያየ ታስሮብኛል ሲል፣ የምስራቅ አፍሪካ የግጭት አጥኝ ቡድን ጋዜጠኞችም ክልከላ ተጥሎባቸዋል፡፡ የእስሩ እና የክልከላው ምክንያት ደግሞ የህወሓት ድምፅ ብቻ ሆነው ወገንተኝነት በማሳየታቸው እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ ብዙዎቹ ጋዜጠኞች ከህወኃት አንዳንዴም ከግብፅ ጋር ወግነው ታይተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የውጭ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ እንድትፈራረስ እየገፋፉ ነው ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ እነ አልጀዚራ የፅንፈኛ ሀይላት ድምፅ ሆነው መክረማቸው አይዘነጋም፡፡ የኢትዮጵያ ሀይል በህወኃት ሀይል ይደመሰሳል የሚል አውድ ያለው ዘገባም አውጥተው ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን በዘራይ አሰግዶም አማካኝነት በብዛት በህወሓት ፍላጎት ይንቀሳቀሱ የነበረ ሲሆን፣ አሁንም የውጭ ሚዲያዎች ወገንተኝነታቸው ለአቶ ዘራይ አሰግዶም አድረገው ሰንብተዋል፡፡ ለአብነት በመተከል 300 አካባቢ ሰዎች ሲያልቁ ለአማራ መስፋፋት የተሰጠ የመልስ ምት አስመስሎ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የሮይተርስ ጋዜጠኞች የካሜራ ባለሙያው ሲታሰር፣ ጋዜጠኞችም ሊከለከሉ እንደሚችሉ ተሰምቷል፡፡ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ሁሉንም ሚዲያዎቿን በኢትዮጵያ ፕረስ ኤጂንሲ ስር አድርጋ በአንድ እዝ ለመምራት እንዳሰበች ይነገራል፡፡ የሁሉም የመንግስት ሚዲያ የቦርድ ሰብሳቢዎች የብልፅግና ፅህፈትቤት ሀላፊዎች ወይም አለቆች ናቸው፡፡ የመረጃ ፍሰት በብልፅግና ሀይል ብቻ እንዲገባ እየተሰራ ሲሆን፣ ማህበራዊ ሚዲያውንም ተከፋይ ብልፅግናዎች እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ፡፡ ከብልፅግና ወገን ያልሆነውን ማሰር የሚያስችል ህግ ረቆ ተግባራዊነቱ እየተጠበቀ ነው፡፡ ሚኒስትሮች ከብልፅግና ፈቃድ ውጭ መፃፍ እንደሌለባቸው ከማስጠንቀቂያ ጋር እግድ ተሰጥቷቸዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply