የውጭ ምንዛሬ ማሻቀብ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 30፣ 2013ዓ.ም) በአምስት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ የብር የመግዛት አቅም በዕጥፍ የወረደ ሲሆን፣ አዲስ የብር ኖት ቅያሬውም መሰረ…

የውጭ ምንዛሬ ማሻቀብ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 30፣ 2013ዓ.ም) በአምስት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ የብር የመግዛት አቅም በዕጥፍ የወረደ ሲሆን፣ አዲስ የብር ኖት ቅያሬውም መሰረ…

የውጭ ምንዛሬ ማሻቀብ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ( አሻራ ታህሳስ 30፣ 2013ዓ.ም) በአምስት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ የብር የመግዛት አቅም በዕጥፍ የወረደ ሲሆን፣ አዲስ የብር ኖት ቅያሬውም መሰረታዊ ለውጥ አላመጣም፡፡ በመደበኛ የባንክ ምንዛሬ 40 ብር አንድ ዶላር ብቻ የሚገዛ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያ ግን አንድ ዶላር እስከ 60 ብር እየተገዛም ይገኛል፡፡ ያነጋገርናቸው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ለአሻራ እንደተናገሩት የውጭ ኢንቨስትመንት አለመኖር፣ ኢትዮጽያ የምስታስወጣው እና የምታስገባው አለመመጣጠኑ እና ኢ- መደበኛ መንግስታዊ መዋቅር መፈጠሩ የሀገሪቱን ብር እያረከሰው ይገኛል ብለዋል፡፡ የሙስና መስፋፋት እና የፋይናንስ ተቋማት የተጠና አሰራር አለመከተላቸው የብርን ዋጋ እየቀነሰ የዶላርን ዋጋ አንሮታል፡፡ በዚህ ከቀጠለ የብር ዋጋ እንደ ዝንባብዌ ገንዘብ ወርዶ በኬሻ መገበያየት ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ሀገራዊ ቀውሱ ከፍተኛ ይሆናል፡፡ መድሃኒት እና ሌሎች መሰረታዊ ሸቀጦችን ለማስገባት የዶላር ዋጋው አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ሀገሪቱ ያለችበት የግጭት ሁኔታም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እያዳከመው ሲሆን፣ እንደ አይኤምኤፍ ግመታ ኢትዮጵያ በ2021 የምታስመዘግበው ዕድገት አይኖርም፡፡ በወለጋ፣በጉራፈርዳ፣በትግራይ፣ በመተከል እና የአንበጣ መንጋው በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ጎን ስላሳደረ ረሃብ በኢትዮጵያ ሊመጣ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply